ልጆች በጨዋታ ውስጥ ባህላቸውን እንዲያውቁ ይረዳል የተባለለት ፌስቲቫል ሊጀምር ነው ተብሏል፡፡

ልጆች በሚጫወቱት ጨዋታ ውስጥ የሃገራቸውን ባህል ጠንቅቀው እንዲያውቁ ይረዳቸዋል የተባለለት”ፌሽታ ኪድስ “የተሰኘ ፌስቲቫል በጊዮን ሆቴል ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በታህሳስ 13 እና 14 የሚደረገው ይህ ፌስቲቫል ከ 3 እስከ 16 የእድሜ ክልል ያሉ ልጆችን መታደም የሚችሉበት እንደሆነ የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ኤቫ ሊግዠሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር አስታውቋል፡፡

ለሁለት ቀን በሚቆየው ፌስቲቫልም ከ5 ሺህ በላይ ልጆች ይታደሙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኤቫ ሊግዠሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር ባለቤት እና መስራች ወ/ሪት ቃልኪዳን ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

ልጆች ከቤተሰቦቻቸው ሆነ ከማህበረሰቡ ጋር ጥሩ ማህበራዊ መስተጋብር እንዲኖራቸው እና ባህላቸው እንዲያውቁ ይረዳል በተባለለት በዚህ ፌስቲቫል የልጆች መጫወቻ ቁሳቁሶች፤ ይሳተፉበታል፡፡

ለገና በአል የተዘጋጁ ጨዋታዎች፤ ውድድሮች እና የሰርከስ ትርኢቶችም እንዳሉ ወ/ሪት ቃልኪዳን ገልጸዋል፡፡

በልጆች ላይ አተኩረው ከሚሰሩ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጋር እንደሚሰራ የገለጸው ኤቫ ሊግዠሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር በልጆች ላይ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች የልምድ ልውውጥም ይደረጋል ብሏል፡፡

ፌስቲቫሉ ታህሳስ 13 እና 14 ማለትም ቅዳሜ እና አሁድ የሚደረግ ሲሆን፤መግቢያ ለልጆች 250 ብር ሲሆን ወላጆች በነጻ እንደሚገቡ ተግልጿል፡፡

መሳይ ገ/መድህን
ታህሳስ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.