የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ተቃዉሞ እንዳጋጠመው ገለፀ።

ኮሚሽኑ ቅሬታን በተመለከተ የሚመለከተዉም የማይመለከተዉም  ቅሬታዎች እንደሚደርሱት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል።

በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቅሬታ አያያዝ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ብዙነህ አሰፋ ከጣብያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በተለይም ፖርቲዎች እኛ የወከልነዉ ማህበረሰብ በምልመላ ሂደት ዉስጥ አልተሳተፉም የሚል ቅሬታ ማንሳታቸዉን ይናገራሉ።

ልየታዉ ይበልጥ የመንግስት ደጋፊ ለሁኑ አካላት የሚያዳላ ነዉ የሚሉ ክሶች ተደጋጋሚ መኖራቸዉንም ለጣብያችን ተናግረዋል።

የቡድን መሪዉም የቀረበዉ ቅሬታ ትክክል ነዉ የሚል አመኔታ እንዳለቸዉም ተናግረዋል።

የምክክር ኮሚሽን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚመለከተዉ የመሳተፍ መብት ያለዉ ነዉ ያሉ ሲሆን ሀገርን እየመራ ያለዉ የመንግስት ፖርቲም ሆነ ተፎካካሪ ፖርቲዎችን የሚወክለዉ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በየወረዳዉ አንድ አንድ ተወካይ እንዲልክ መደረጉን አስርደተዋል።

በአሁን ሰዓት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገርን ወክለዉ አጀንዳ የሚሰጡ አካላትን የመለየት ስራ እየተሰራ ነዉ ብሏል።

ነገር ግን እስካሁን ባለዉ አጀንዳ ልየታም ሆነ ምክክር አልተጀመረም ሲሉ የቡድን መሪዉ ለጣብያችን ተናግረዋል።

ታህሳስ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
በአቤል ደጀኔ

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.