ስዊዘርላንድ በጋዛ ላሉ ህጻናት የ11.5 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አደረገች፡፡

ስዊዘርላንድ በዩኒሴፍ በኩል ለጋዛ ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸዉ የሚዉል የ11.5 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አናዶሉ አስነብቧል፡፡

የስዊዘርላንድ የልማት እና ትብብር ኤጀንሲ በጋዛ ያለዉ ጦርነት በህጻናት እና በቤተሰቦቻቸዉ ላይ የሚያደርሰዉ ጉዳት አስከፊ ሆኖ ቀጥሏል ብሏል፡፡

ኤጀንሲዉ ለዩኒሴፍ የሰጠዉ የገንዘብ ድጋፍ ለህጻናቱ እና ቤተሰቦቻቸዉ የዉሃ፣ የንጽህና፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ ጤና ፣ምግብ እና ትምህርት ላይ የሚዉል መሆኑንም ገልጿል፡፡

እስራኤል በጥቅምት 7 በሃማስ የደረሰባትን ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት ተከትሎ በአየር እና በምድር እያደረሰች ባለችዉ ድብደባ ህጻናት እና ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለዉ ጉዳት አስከፊ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚገልጸዉ እስካሁን በጥቃቱ ከ19ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን የተገደሉ ሲሆን ፤ ከ52ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በሃማስ ጥቃት እስካሁን 1ሺህ 2መቶ እስራኤላዊያን የተገደሉ ሲሆን ከ1መቶ30 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታግተዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.