በተያዘለት ቀን ያልተሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ፈተና በቀጣይ ቅዳሜ ይሰጣል ተባለ

አጋጥሟል በተባለ የቴክኒክ ችግር ሳቢያ ሳይሰጥ የቀረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ፈተና በቀጣይ ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞችን ብቃት እና ባህሪ ለመመዘን በሚል ከ16 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፈተና እንደሚቀመጡ ቢገለጽም ፈተናው ሳይሰጥ መቅረቱ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ባጋራው መረጃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ባሳለፍነው ሳምንት ፈተናውነ ለመውሰድ በመፈተኛ ቦታዎች በመገኘት በትዕግስት ሲጠባበቁ የነበሩትን የአስተዳደሩን ሰራተኞች ለደረሰባቸው መጉላላት ቢሮው ይቅርታ ጠይቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.