አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለ17 የላዳ አሽከርካሪዎች አዲስ መኪናዎችን አስረከበ

አሚጎስ ብድር እና ቁጠባ ለ3ኛ ዙር ለላዳ መኪና አሽከርካሪዎች የመኪናውን 30 በመቶ ለቆጠቡ 17 አሽከርካሪዎችን አዲስ መኪናን በዛሬው እለት አስረክቧል።

የአሚጎስ ብድር እና ቁጠባ የኮርፖሬት ሴልስ ክፍል ሀላፊ አቶ እንዳልካቸው በሀይሉ እንደገለፁት በአሁን ሰአት 35 የላዳ ማህበራት ከተቋሙ ጋር ውል ተዋውለዋል ።

ተቋሙ በዛሬው እለትም የመኪናውን ዋጋ 30 በመቶ መቆጠብ የቻሉ 17 የላዳ አሽከርካሪዎች ኦክሎክ ጀነራል ትሬዲንግ የሚያስመጣቸውን መኪኖች ማስረከቡ ተገልጿል።

የብድር የክፍያ ጊዜውም ለ10ዓመት እንደሚቆይ እና የወለድ መጠኑም ከ9 እስከ 15 በመቶ እንደሆነም ተነግሯል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በ11 ዓመት ውስጥ 3ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የብድር አቅርቦት እንደሰጠ እና ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ለተሽከርካሪ መግዣ የተሰጡ መሆናቸው ተገልጿል።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር አሁን ላይ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ካፒታል ላይ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን 7000 የሚደርሱ አባላት አሉት።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በአዋጅ ቁጥር 147/91 እና ይሄንን አዋጅ ለማሻሻል በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 402/96 መሰረት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ነዉ፡፡

ማህበሩ ላለፋት አስር አመታት ለ 3000 ሰዎች የብድር አገልግሎትን በመስጠት በርካቶች ስራቸውን እንዲያስፋፉ እና ስራ እንዲፈጥሩ ማድረጉ ተገልጿል።

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *