የውድድር ስፍራዎች የሚከሰቱ የጸጥታ መደፍረሶችን ለማስተካከል የሚመለከተው የአገሪቱ የጸጥታ አካል ለሚወስዳቸው ማናቸውም ህጋዊ እርምጃዎች ተባባሪ ነኝ አለ የኢትዮጲያ ቡና ክለብ ደጋፊዎች ማህበር

የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም ከዘንድሮ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ጅማሮ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በሚሳተፍበት በታላቁ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እንዳይሳተፍ የቦርድ ሊቀመንበር፣ የክለቡን ስራ አስኪያጅ፣ የደጋፊ ማህበሩን ስራ አስፈጻሚዎችን፣ አስተባባሪዎችን እና ለስታዲየማችን ድምቀት በመሆን አስጨፋሪዎች ለክለቡ ውጤት የሚለፉትን ያለ በቂ ማስረጃ በመዝለፍ እና በማስፈራራት ስራ እንዳይሰራ መከልከል ስራዎች ላይ ጥቂት ደጋፊዎች ተሰማርተው ተገኝተዋል ብሏል።

በማህበራዊ ሚዲያና በውድድር ስፍራዎችም በተቀናጀና ከፍተኛ ድጋፎችን በማስተባበር ከስም ማጥፋት እስከ ንብረት የማውደምና ክለቡን ለከፍተኛ የህልውና አደጋ እየዳረጉት ይገኛሉ ብለዋል በመግለጫው።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር እስካሁን የተጓዘባቸው ርቀቶች መፍትሄ ለማምጣት ባለመቻላቸው ከዚህ በኋላ ክለባችን ጨዋታ በሚያደርግባቸው የውድድር ስፍራዎች የሚከሰቱ የጸጥታ መደፍረሶች ለማስተካከል የሚመለከተው የአገሪቱ የጸጥታ አካል ለሚወስዳቸው ማናቸውም ህጋዊ እርምጃዎች ተባባሪ መሆኑን ያስታውቃል ሲል አስተንቅቋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያያዎች ላይ የተለያዩ የስም ማጥፋት እና ደጋፊዎችን ላልተፈለገ አመጽ የሚገፋፉ በስመ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊነት ሽፋን ህገ-ወጥነትን የሚያበረታቱ ጥቂት ግለሰቦችን ቡድኖችን የሚመለከተው የፀጥታ ኃይሉ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ቅድመ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን እናሳውቃለን ሲል አሳስቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.