አማራ ባንክ በበጀት ዓመቱ የ481 ሚሊየን ብር ኪሳራ እንዳጋጠመው አስታወቀ።

ባንኩ በተለያዩ ወጪዎች ምክንያት በአመቱ መጨረሻ ላይ ኪሳራ ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

ባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠኔ ከ28 ቢሊየን ብር በላይ ደርሷልም ብሏል።

የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም 5.8 ቢሊየን ብር ደርሷል።
ባንኩ በ2015 የሂሳብ አመት ጠቅላላ የሀብት መጠኑ 28.4 ቢሊየን ብር መድረሱን አስታውቋል።

በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም የሂሳብ ዓመት ከ1መቶ ሺህ በላይ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎችን መድረስ የቻለ ሲሆን ፤ አጠቃላይ ገቢውም ከ1.8 ቢሊየን ብር በላይ ሆኗል ነው የተባለው።

ባንኩ ከ1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን፤ ከ14.9 ቢሊየን ብር በላይም ብድር አቅርቧል።

በ2015 የሂሳብ ዓመት የቅርንጫፍ ቁጥሬን ከ290 በላይ አድርሻለሁ ያለው ባንኩ፤ ከ19.8 ቢሊየን ብር በላይ የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል።

አማራ ባንክ ከ140 ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች በብር 4.8 ቢሊየን የተከፈለ ካፒታል እና በብር 6.5 ቢሊየን የተፈረመ ካፒታል ከአንድ አመት በፊት ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

ባንኩ በዛሬው ዕለት ሁለተኛውን የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በጎልፍ ክለብ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በእስከዳር ግርማ
ታህሳስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.