በአማራ ክልል ያለዉ የፀጥታ ችግር የግብርና ስራዉን ቢያሰተጓጉልም 5.1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሰብል መሰብሰቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ የተከሰተዉ የፀጥታ ችግር የሰብል ማሰባሰብ ሂደቱን እንዳስተጓጎለዉ የገለጸዉ ቢሮዉ ከ5.1ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 4 ሚሊዮን ሄክታር የሚሸፍን ሰብል መሰብሰቡን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምሳሉ አበበ በተከሰተ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብና በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ስራው ቢስተጓጎልም በተደረገው የህዝብ ንቅናቄና ትብብር ሰብል የመሰብሰብ ስራውን እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል ።

በአማራ ክልል ከ2015_16 የመኸር ምርት ዘመን 5.1ሚሊዮን ሄክታር መሬት ማሳ በዘር እንደተሸፈነ እና 160 ሚሊዮን ኩምታል ምርት ለማምረት እቅድ መታቀዱንም አስታዉሰዋል፡፡

የግብርናዉ ዘረፍ እንዳይጎዳ ሁሉም ባለድርሻ በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን በትኩረት መስራት እንዳለበት አቶ አምሳሉ ጠይቀዋል፡፡

በሀመረ ፍሬው

ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.