አይደር ስፔሽያላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ሊያካሂድ መሆኑ ተገለጸ፡፡

• በዚህ ቴሌቶን እስከ 200 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዷል ተብሏል

አይደር ሪፈራል ሆስፒታል በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ትልቁና በአመት እስከ 300ሺህ እና ከዛ በላይ ታካሚዎችን ያስተናግድ የነበረ ነው፡፡
ይህ ታላቅ ሪፈራል ሆስፒታል በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የቁሳቁስና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት አጋጥሞት ህመምተኞችን ለማከም በእጅጉ እየተፈተነ መሆኑ ይነገራል፡፡

አይደር ሪፈራል ሆሶፒታልን እንታደግ በሚልም ታላቅ ዓለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን፤ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም፤ በ መቀሌ ኖርዘርን ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል።

በመቀሌ ዮኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል አልሙናይዝድ የቀድሞ ተማሪዎች አስተባባሪነት የተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ ማህበረሰቦችን የሚያካትት እንደሆነ ተነግሯል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአይደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ብርሀነ ገብረ ሚካኤል፣ ሆስፒታሉ እንደ መጀመሪያ የተወሰነ ገቢ ካገኘ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ስራዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ወደስራ ለመግባት እንዳቀዱ እና የሚደረገው የገቢ ማሰባሰቢያም ለስራቸው እገዛ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል።

በዓለማቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያው ከአንድ መቶ እስከ ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ለማግኘት እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ እና
ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በዚህ የበጎ አድራጎት ተግባር ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በሀመረ ፍሬው
ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.