የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሰራተኞች ለመስጠት ያሰበው ፈተና እሣት የማጥፋት አካሄድ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡

አንድ የመንግስት ሰራተኛ የሚመዘንበት እራሱን የቻለ አሰራር እያለው ህጋዊ ስርዓትን ባልተከተለ የፈተና ስርዓት ሰራተኛውን ማጉላላት ተገቢ አይደለም ሲሉ የኢህአፓ ተቀዳሚ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አንድ ሰራተኛ በስራው ድክመት ካሳየ የተለያዩ የስልጠና መንገዶችን በመጠቀም ስልጠና መስጠት የተሸለ አማራጭ ሆኖ ሳለ በብዙ ችግር ውስጥ የሚዳክረውን የመንግስት ሰራተኛ በዚህ ደረጃ እንዲጉላላ የሚደረግበት መንገድ እንደሳዘናቸው ሊቀመንበሩ ለጣብያችን አስርድተዋል፡፡

ሰራተኛው ከዚህ ቀደም በሙስና ብልሹ አሠራር እንዲሁም በጎጥ አጥር ስር በመሆን ጥፋቶችን ሲያጠፋ በወቅቱ የእርምት እርምጃ ሳይወሰድ ቆይቶ አሁን እሣት የማያያዝ ስራ ለመስራት መረባረብ ችግሩን መፍትሄ አያስገኝለትም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ሰራተኛውን ሀገር ወዳድ በማድረግ ከጎጠኝነት አስተሳሰብ ማላቀቅ እንደሚገባ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ኢህአፓ በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ከማውጣት የተቆጠበውም አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ከመግለጫ በላይ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመሆኑ ነው ብለውናል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.