መንግስት እና የሶማሊላንድ የፈረሙት የመግባቢ ሰነድ በቀጠናው የውጥረት መንገስ ምክኒያት እንዳይሆን ያሰጋል አለ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፡፡

በአካባቢው ያሉት ሁሉም አካላት ውጥረቱን በሰከነ አካሄድ እንዲፈቱት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡ በተለይም ለስደተኞች እና ሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ ሊደረግ ይገባልም ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እና የሶማሊላንድ ግዛት ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈረሙ ሰበብ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ዉጥረት መቀስቀሱ እንዳሳሰበው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ለሚ ገመቹ ገልጸዋል፡፡

በአከባቢው ሁሉም አካላት ውጥረቱን በሰከነ አካሄድ እንዲፈቱት ባወጣነው መግለጫ ጠይቀናል ያሉት ከኤትዩ ኤፍ ኤም ጋር ቁይታ ያደረጉት አቶ ለሚ ፤ በተለይም ለስደተኞች እና ሰላማዊ ዜጎች ጥበቃ ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው ቀደም ብሉ ባወጣው መግለጫ ከዚህ በፊትም በሁለቱ አገራት መንግስታት መካከል በተፈጠረ ችግር በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተለይም ሶማሊያ ውስጥ በተጠለሉ የኦሮሞ ስደተኞች ላይ ተደጋጋሞ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል፡፡

አቶ ለሚ እንዳብራሩት የኦሮሞ ህዝብ ከጎረቤት የሶማሊያ ህዝብ ጋር ለዘመናት ባህል፣ ወግ፣ ሃይማኖት እና ድንበር ተጋርቶ በሰላም መኖሩን ያወሳው ኦነግ በገዢዎች ተደጋግሞ በሚቀሰቀስ ግጭት ግን የሰው ህይወት እና ሃብት ስወድም መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡

ስለሆነም ወንድም ህዝብ በሆነው የሶማሊያ ህዝብ መካከል ለፍትህ እና ሰብኣዊ መብት መከበር ያደላ አዎንታዊ ግንኙነት ያለ በመሆኑ የጋራ ሰብኣዊ እሴት ያለው ይህ ግንኙነት እንዳይበላሽ የሶማሊያ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ህዝብ አንቂዎች ጥሪ እንዲያሰሙም ፓርቲያቸው መየቁን ነግረውናል፡፡

የኦነግ ህዝብ ግንኙነቱ አቶ ለሚ በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ በሶማሊያ ውስጥ ኑሮውን እንደመሰረተ አስታውሰው ውጥረቱ በጠነከረ ቁጥረም ልክ እንደዚህ ቀደሞ ሰላማዊ ዜጎች የጥቃት ኢላማ እንዳይሆኑ ከወዲሁ ጥንቃቂ እንዲደረግ ለማሳሰብ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.