ደቡብ አፍሪካ እስራኤል ለሃማስ ዘመቻ የሰጠቸው ምላሽ የዘር ማጥፋት ስምምነትን የሚጥስ ነው አለች፡፡

በሄግ የሚገኘው አለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት /ICJ/ በጋዛ ጉዳይ ላይ የፍልስጤሙ ሀማስ ቡድን ለከፈተው ጥቃት እስራኤል የሰጠቸው ምላሽ የዘር ማጥፋት ስምምነትን ጥሷል ስትል ደቡብ አፍሪካ ተናግራለች፡፡

በሄግ የሚገኘው የተባበሩር መንግስታት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐሙስ ዕለት ደቡብ አፍሪካ እስራኤል የዘር ማጥፋ ስምምነትን በመጣስ በጋዛ ህዝብ በሚበዛበት ቦታ ላይ ከሁለት ወራት በላይ አሰቃቂ ጦርነት አድርጋለች ብሏል፡፡

እስራኤል ይህንን ምላሽ የሰጠውት የሀማስን ወረራ ለመቀልበስ ነው ማለቷ ተቀባይነት የሌለው ነውም ብላለች ደቡብ አፍሪካ፡፡

ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ ፕሪቶሪያ በእሰራኤል ላይ ለአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ባቀረበቸው 84 ገፅ ክስ ቴላቪቭ ቀጣይነት ያለው ጦርነት ከከተፈተችበት ግዜ አንስቶ አለም አቀፍ ህጎችን መጣሷን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ጠይቃለች፡፡

የእስራኤል ጋዛ ጦርነት ከተነሳ ጀምሮ የእስራኤል ጦር በትንሹ 23,210 ፍልስጤማውያንን በአብዛኛው ህፃናት እና ሴቶችን መገድና 59ሺህ 167 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የፕሬስ ቲቪ ዘገባ ያሳያል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጥር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.