በኢትዮጵያ ከ3 ነጥብ 45 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ከ3.45 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በግጭት ምክንያት መፈናቀላቸውን የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አዲስ ሪፖርት አመልክቷል።

በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የተሰበሰበ መረጃ እንደሚያሳየው በስደት መከታተያ በኢትዮጵያ ከ3 ነጥብ 45 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በግጭት ሳቢያ መፈናቀላቸውን ይገልፃል።

አይ ኦ ኤም የመፈናቀል ዋና መንስኤዎች ብሎ ያስቀመጣቸው ግጭት 64 በመቶ፣ ድርቅ 17 በመቶ እና ማህበራዊ 9 በመቶ መሆናቸውን አመልክቷል።

የሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት ከፍተኛውን የተፈናቃዮች ቁጥር የያዘ ሲሆን ትግራይ ክልል ደግሞ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉትን ከፍተኛ ቁጥር ይይዛል።

በሪፖርቱ እንደተገለፀው በ11 ክልሎች ውስጥ ከ2,000 በሚበልጡ መንደሮች ውስጥ ወደ 2.53 ሚሊዮን የሚገመቱ ተፈናቃዮች መለየታቸውም ተመላክቷል።

ከተለዩትም ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛው ተፈናቃዮች የተመለሱት በትግራይ ክልል 59 በመቶ፣ አማራ 15 በመቶ እና አፋር 8 በመቶ ናቸው።

አይ ኦ ኤም ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የተፈናቃዮችን እና ከስደት ተመላሾችን ቁጥር እንዲሁም አካባቢያቸውን እና ፍላጎታቸውን በመያዝ አካባቢን መሰረት ባደረገ ግምገማ የሰብአዊ እና መፈናቀል ሁኔታን ይከታተላል።

ለአለም አሰፋ
ጥር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *