የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት ተነሳ

የአማራ ክልል ምክር ቤት በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ ዮሐንስ ቧያለውን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

የክልሉ ምክር ቤት፤ የምክር ቤቱ አባል የነበሩትን የአቶ ዮሐንስ ቧያለው ያለመከሰስ መብት ያነሳው እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ መሆንን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የሁለት ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የ154 የወረዳ ረዳት ዳኞችን ሹመት አጽድቋል። በዚህም መሠረት አቶ ባየ ጌታቸው ፈንታ የምሥራቅ ጎጃም ዞን እና አቶ ዮሀንስ ወንድሙ ደስታ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኾነው ተሾመዋል። የ154 የወረዳ ረዳት ዳኞች ሹመት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል ተብሏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *