የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር በዛሬው ዕለት ጠርቶት የነበረው መግለጫ ተሰረዘ፡፡

ማህበሩ በዛሬው ዕለት ጠርቶት በነበረው መግለጫ “ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊስ እና አስተዳደር በኢትዮጵያ ስኬቶቹ፣ተግዳሮቶቹ እና ተፅኖዎቹ” በሚል ርዕስ መነሻ ላይ መግለጫ ለመስጠት ነበር፡፡

መግለጫው ለምን እንደተሰረዘ ማህበሩ ከመግለፅ የተቆጠበ ሲሆን፣ መግለጫውን ለመከታተል በቦታው የተገኙ ጋዜጠኞች እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡

በዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሊቀርብ የተዘጋጀው የጥናት ወረቀትም ለጋዜጠኞች ከተበተነ በኃላ እንዲሰበሰብ መደረጉን ጣቢያችን በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል፡፡

ጥናቱ በኢትዮጵያ ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን እና የኢኮኖሚ ድክመቶችን ለመገምገም ያለመ ነበር ተብሏል፡፡

የአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ እና የዘላቂ ልማት ግቦች እድገትን መተንተን፣በኢትዮጵያ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋትና ተለዋዋጭነት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊዳሰሱ የታሰበበት መድረክ መዘጋጀቱን ባደረግነው ማጣራት ለመታዘብ ችለናል፡፡

በእነዚህ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለመመክር የተሰየመው ማህበሩ በዛሬው እለት የሚሰጠውን መግለጫ ምክንያቱን ሳይገልፅ በመዘረዝ ላልታወቀ ጊዜ መግለጫው መተላለፉን ቦታው ላይ በመገኘት መመልከት ችለናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ምክንያቱ ምን ይሆን? በሚል ባደረገው ማጣራት የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሚያነሳቸው ጉዳዮች ጠንከር ያሉ መሆናቸው ጋዜጣዊ መግለጫው ዛሬ እንዳይሰጥ መደረጉን ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጮች አረጋግጠውልናል፡፡

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *