በስድስት ወር ከደረሱ የእሳት አደጋዎች መካከል 15ቱ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሱ ናቸው ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2016 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በስድስት ወራት የደረሱትን የ139 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት 73 ቃጣሎ፣ በመካኒካል ችግር 19፣ ኢንሹራንስ ለማግኘት፣ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ወይም ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ለማድረስ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 15፣ በቸልተኝነት 15 እና በሌሎች ምክንያቶች 8 መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ከደረሱት አደጋዎች ውስጥ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ወይም ሌላ ሰው ላይ ጉዳት ለማድረስ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሱት የእሳት አደጋዎች 15 ናቸው ሲል ፌደራል ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ከተከሰቱት 139 የእሳት ቃጠሎዎች፤ 130ዎቹ በአዲስ አበባ፤ ዘጠኙ ደግሞ በክልሎች የተከሰቱ መሆናቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ቃጠሎ ከደረሰ ጉዳቱን ለመቀነስ ማጥፋት ተገቢ ቢሆንም፤ ከጠፋ በኋላ ግን መረጃው እንዳይጠፋ ቦታው ሳይነካካ ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

ቃጠሎው በፎረንሲክ ምርመራ እስካልተረጋገጠ ድረስ የደረሰው በዚህ ምክንያት ነው ብሎ መፈረጅ፤ ምርመራውን አስቸጋሪ ከማድረጉም በላይ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርም ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *