ለ 48 ሺህ 7መቶ ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከፊታችን ማርች 8 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አስመልክቶ በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንፃር ለ 48ሺህ 7መቶ ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠሩን ቢሮው ለኢትዮ ኤፍኤም አስታውቋል።

ቢሮው በቀጣይ ለ 36 ሺ ሴቶች የስራ እድል ለመፍጠር እቅድ መያዙንም ገልፃል፡፡

የሴቶችን ገቢ ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ የተገለፀም ሲሆን ለ አንድ ሴት 10 ሺ ብር በማበደር በጠቅላላ የ 10 ሚሊየን 510 ሺ ብር በጀት መያዙን ተሰምቷል፡፡

የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ቢሮ በቁጠባ ፤ ምንም ገቢ ለሌላቸው፤ ለጤናማ እናትነት፤ በሴፍትኔት ፕሮግራም፤ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እና በሌሎችም ዘርፍች ላይ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስተውቋል፡፡

የዘንድሮ አለም አቀፍ የሴቶች ቀንም ‘’ ሴቶችን እናብቃ ፣ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ ” በሚል መሪ ዋል እንደሚከበር የአዲስ አበባ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በሀገራችን ለ48ኛ ጊዜ በዓለማችን ደግሞ ለ113ኛ ጊዜ እንደሚከበር ይከበራል።

በልዑል ወልዴ

የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *