ቀድሞ በፒያሳ እና አከባቢው አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አስር የከተማ አውቶብስ መስመሮችን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በአንድ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።

የአደዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ባሻገር ህብረተሰቡ ደህንነቱ ተጠብቆ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኝበትን የከተማ አውቶብስ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በትራንስፖርት ቢሮ የአራዳ ቅርንጫፍ
ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አርጋው በቀለ የከተማ አስተዳደሩ ለትራንስፖርቱ መስኩ በሰጠው ትኩረት መነሻነት ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመሆን የብዙሀን ትራንስፖርት ተጀምሯል ብለዋል።

ቀድሞ በፒያሳ እና አከባቢው ሲሰጡ የነበሩ አስር የከተማ አውቶብስ መስመሮችን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም በአንድ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ብለዋል።

ህብረተሰቡም በሙዚየሙ ምስራቅ ጀግኖች በር በመግባት ወደ አየር ጤና፣ ካራ ቆሬ፣ ቦሌ ቡልቡላ፣ ሳሪስ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ፣ አጃምባ፣ ጀሞ 3፣ ሃና ማርያም፣ ቱሉዲምቱ እና ዩኒሳ የሚሄዱ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *