የምክክር ኮሚሽኑ በጅማ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ በጅማ ክላስተር የ114 የወረዳና የከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች በአጀንዳ ማሰባሳቢያ ህዝባዊ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የሚመርጡባቸው መድረኮችን እያካሄደ ነው፡፡

እስከ ትናንት ድረስም 57 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተወካዮቻቸውን መምረጥ ችለዋል፡፡ በሂደቱ ከ4ሺ 500 በላይ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል ብሏል ኮሚሸኑ፡፡

የጅማ ክላስተር የጅማ ዞንን ጨምሮ፣ ከቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞኖች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች በአጀንዳ ማሰባሳቢያ ህዝባዊ መድረኮች ላይ የሚሳተፉ ተወካዮቻቸውን የሚመርጡበት ክላስተር ነው፡፡

እስከ ትናንት ድረስ ባለው ሂደት ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦርና ምሥራቅ ወለጋ የመጡ  የ56 ወረዳዎች ተሳታፊዎች ተወካዮቻቸውን መርጠዋል፡፡

መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *