እስራኤል የኢራኑን የጦር መኮንን መግደሏ ተነገረ

የእስራኤል አየር ሃይል በሶሪያ ወሰደ በተባለዉ ጥቃት ከፍተኛ የኢራን የጦር መኮንን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸዉ ቴህራን አስታዉቃለች፡፡

የኢራኑ አብዮታዊ ዘብ ጠባቂ አመራር የነበረዉ ብርጋዴር ጀነራል ሙሃመድ ሬዛ ዛሂዲ በሶሪያ ደማስቆ ከተማ በሚገኝ የኢራን ቆንስላ ጽህፈት ቤት መገደሉ ተነግሯል፡፡

ኢራን ለእስራኤል ጥቃት እጅግ የከፋ አፀፋዊ እርምጃ እንደምትሰጥ እየዛተች ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁሴን አሚር አብዱላሂያን የበቀል እርምጃ በአስራኤልና በአሜሪካ ላይ ይወሰዳል ነዉ ያሉት፡፡

ጥቃቱን ተከትሎ የኢራንና የእስራኤል ዉጥረት አደገኛ ሁኔታ ላይ እንዳይደርስ ተሰግቷል፡፡

እስራኤል የኢራኑን ከፍተኛ የጦር መሪ መግደሏን ተከትሎ ኢራን የመልስ ምቱ የከፋ ነዉ እያለች ነዉ፡፡

የሶሪያ መንግስትም ጥቃቱን የሽብር ጥቃት ሲል አዉግዞታል፡፡ ይሁን እንጅ እስራኤል ስለ ጥቃቱ ያለችዉ ነገር የለም፡፡

ከሃማስ ጥቃት ጀርባ ኢራን አለች በሚል እስራኤል ስትከሳት እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡

አባቱ መረቀ

መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *