የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ጸድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 19ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተሰፋዬ በልጅጌ እንደገለጹት፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና እና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊነትን በተመለከተ ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡ ሲሆን፣ በአስፈላጊነቱም ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ምክንያታዊ ያልሆነ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጨማሪን በማስቀረት፣ በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጫና የሚያቃልልና ህጋዊ አሰራርን ለመከተል ጠቃሚ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

የኑሮ ውድነቱን እያባባሱ ካሉ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የቤት ኪራይ መጨመር አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለችግሩ እልባት ለመስጠት ህግና አሰራር ማበጀት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሰራሩ መሰረትም በተከራይ እና አከራይ መካከል ስለሚኖረው ውል የውሉን ተፈፃሚነት የሚቆጣጠር አካል የሚኖር መሆኑንም ጠቁመዋል።

መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *