የፌደራል መንግስት እና ህወሃት የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ጀመሩ።

በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የፌደራል መንግስት ልኡክ ዛሬ መቀሌ ገብቷል።

ልኡኩ መቀሌ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ፣ የህውሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል አቀባበል አድርገውለታል።

የመከላከያ እና የትራንስፖርትና ሊጂስቲክ ሚኒስትሮችን ያካተተው የፌደራል መንግስት ልኡክ፣ ከህወሃት እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት ጋር ምክክር ማድረግ ጀምረዋል ነው የተባለው።

የፌደራል መንግስቱ እና ህወሃት የሁለት አመቱን ደም አፋሳሽ ጦርነት ለመቋጨት፣ በፕሪቶሪያ በደረሱት ስምምነት መሰረት፣ በፍጥነት ፖለቲካዊ ውይይት መጀመር ቢኖርባቸውም በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይቷል።

ሁለቱም ወገኖች በመቀሌ ምክክር ሲጀምሩ የፖለቲካዊ ንግግሩ በመደበኛነት እንዲቀጥል መስማማታቸው ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጥር ወር መጨረሻ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ፣ ከህወሃት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ፊት ለፊት መገናኘታቸው ይታወሳል።

በዚህ ምክክርም ሁለቱም አካላት የፖለቲካ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው አይዘነጋም።

መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *