ጀርመን የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አስራለሁ አለች፡፡

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገራችን ድርሽ ካሉ እናስራቸዋለን ብለዋል፡፡

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አባል የሆነችዉ ጀርመን የፍርድ ቤቱን ህግ እንደመረታከብርም አስታዉቀዋል፡፡

እናም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ ጀርመን ከተጓዙ ለእስር እንደሚዳረጉ በርሊን ገልጻለች፡፡

ኦላፍ ሾልዝ ይህንን ዉሳኔ ያሳለፉት በጀርመን የእስራኤል አምባሳደር በርሊን ከድርጊቷ እንድትቆጠብ ማሳሰባቸዉን ተከትሎ ነዉ ሲል አፈርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጋዛዉ ጦርነት ምክንያት በእስራኤሉ ጠቅላ ሚኒስትር ላይ የእስር ማዘዣ እንዲወጣ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ዉሳኔዉን አሳፋሪ ነዉ ብለዋለች፡፡

በአባቱ መረቀ

ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *