በእርግዝና ወቅት የግብረ ስጋ ግንኙነት ቢደረግ ችግር አለዉ?

የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ የአዕምሮ ዝግጁነት ፣አካላዊ ደህንነት ፣የሰዉነት ዉስጥ የሆርሞን አይነቶች መጨመርና መቀነስ እንዲሁም የሌሎች ጉዳዮች ዝግጁነት ያስፈልጋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእርግዝና ወቅት የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት በፅንሱም ሆነ በእናትየዉ ላይ ምንም ጉዳት አያመጣም።
በግንኙነት ወቅትም የወንዱ ብልት ከፅንሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖረዉም። ፅንሱ በእንሽርት ዉሃ፣ በማህፀን ጡንቻ እንዲሁም የማህፀን አፍ በአይን የማይታዩ ተህዋሲያን (microorganisms ) እና የወንድ የዘር ፍሬ እንዳይገባ ሆኖ ዝልግልግ ብሎ ወፈር ባለ ፈሳሽ (mucosal plug)ተዘግቷል።
ፈሳሹም ከግንኙነት በኋላ ወደዉስጥ ሳይገባ ይመለሳል (ይወጣል)።

በቅዱስ ጳዉሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እና በዮኮ የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታል የማህጸን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ሃኪም እና የስነ-ተዋልዶ አካላት ካንሰር ሰብ ስፔሻሊቲ ሲኒየር ፌሎ ከሆኑት ከዶ/ር መሰረት ኦላና ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ ቆይታ አድርገናል፡፡

በእርግዝና ወቅት ሁሉም የሴቶች አካል ላይ የተለያዩ ለዉጦች ይታያሉ፡፡

የግብረ-ስጋግንኙነት ፍላጎት ላይም ለዉጦች እንደሚኖሩ ነዉ ዶክተር መሰረት የሚናገሩት፡፡

ብዙ ሴቶች በዚህ ወቅት ፍላጎታቸዉ ይቀንሳል፡፡ በእርግዝና ወቅት የተለያዩ ህመሞች ስለሚኖሩ ፍላጎታቸዉ በጣም የቀነሰ ይሆናል፡፡ ሌሎች ደግሞ እርግዝና የግንኙነት ፍላጎታቸዉ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይኖረዉም፡፡ በሌላ በኩል ወደ 8 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች ደግሞ የተሻለ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡
የመጀመሪያዉ 3 ወር ላይ እናትየዋ ከፍተኛ የማቅለሽለሽ፣የማስታወክና ስለእርግዝናዉ ትክክለኝነት በጣም የምትጨነቅበት ወቅት ስለሆነ የግብረስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎቷ የቀነሰ እንደሚሆን ነዉ ዶ/ር መሰረት የሚናገሩት፡፡

በዚህ ወቅት ላይ ከትዳር አጋራቸዉ ከፍተኛ ፍቅርና እንክብካቤ የሚፈልጉበት ወቅት ስለመሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ከ3ወር እስከ 6 ወር ጊዜ ባለዉ ደግሞ ቀደም ብለዉ ያሉት ህመሞች ስለሚቀንሱ እና አልፎ አልፎም ስለሚጠፉ፣ የምግብ ፍላጎት ስለሚስተካከል የግብረስጋ ግንኙነታቸዉም እየተስተካከለ የሚመጣ ይሆናል፡፡

እርግዝናዉም የተስተካከለ የሚሆንበት ፤የደም ዝዉዉር ወደ ማህፀን እና ጡት የሚጨምርበት ወቅት ስለሆነ በዚህ ጊዜ ከፍተኛ የግብረስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት ሊኖራት ይችላል።

ከ6ወራት በኋላ ያሉት ጊዜያት ደግሞ ልጅ የተሸከመዉ ማህጸን እድገቱ እየጨመረ ስለሚመጣ፤ ለመተኛትም ሆነ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

በዚህ ወቅት ላይ ታዲያ የተለያዩ ህመሞች ሊከሰቱ ስለሚችሉ ለግንኙነት ያላቸዉ ፍላጎት ተመልሶ ይቀንሳል፡፡

ታዲያ በየትኛዉ ሁኔታ ነዉ የግብረስጋ ግንኙነት መደረግ የሌለበት?

የመጀመሪያዉ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ዉርጃ አጋጥሟት የሚያዉቅ ከሆነ

አንዲት ሴት ከወለደች በኋላስ መች ግንኙነት ብትጀምር ይሻላል?

በዚህም ምክንያት ቀዶ ህክምና አድርጋ ከነበር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድም

ለኢንፌክሽን በማጋለጥ ሌላ ዉርጃ እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል

በተለያየ ምክንያት በማህጸን በኩል ደም ካየች /በመሰረቱ አንድ እናት በእርግዝና ወቅት በፍጹም መድማት የለባትም አልያም የደም ምልክት ማየት የለባትም/

እንግዴ ልጅ ከልጅ ቀድሞ ከመጣ እና በዚህ ወቅት ግንኙነት ቢደረግ የወንድ ብልት የማህጸን ጫፍን ሊነካ ስለሚችል እና በዚህ ምክንያትም መድማት ስለሚኖር በዚህ ወቅት ግንኙነት ማድረግ አይመከረም

ቀኑ ሳይደርስ የእንሽርት ዉሃ ከፈሰሰ ግንኙነት መደረግ የለበትም ምክንያቱም የተለያዩ ባክቴሪያዎች ወደ ዉስጥ እንዲገቡ ስለሚያመቻች እና ኢንፌክሽን ስለሚፈጥር መደረግ የለበትም

ሌላዉ ቀኑ ያልደረሰ ምጥ ካለ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ አይመከረም ይህም ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ይችላል

የመጀመሪያዉ እና ወሳኙ ጉዳይ ግን ግንኙነት የማድረግ ፍላጎቷ ነዉ፡፡ ፍላጎት ደግሞ ወዲያዉ አይመለስም፡፡

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዲት ሴት ከወለደች 21 ቀናት አልያም ሶስት ሳምንት በኋላ ፍላጎቷ ይመለሳል፡፡

ዶክተር መሰረት በመጨረሻም በእርግዝና ወቅት ለሚደረግ የትኛዉም ግንኙነት ባለሙያን ማማከር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *