ጣሊያናዊው የ54 ዓመቱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ በይፋ አዲሱ የናፓሊ አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እስከ 2027 ለሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይፋ ሆኗል።

” የናፖሊ አሰልጣኝ በመሆኔ ደስታ ተሰምቶኛል ክለቡን ለማሳደግ እና ቡድኑን ለማሻሻል ያለኝን ሁሉ እንደምሰጥ ቃል እገባለሁ።”ሲሉ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

በጋዲሳ መገርሳ

ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *