የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአደባባይ ቅርሶች አይፈርሱም እያለ በጎን ግን አፍራሽ ግብረ ሃይል እየላከባቸው መሆኑን ፒያሳ አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች ተናገሩ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ከሰሞኑ የከተማዋ አስተዳደር ከመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት ውስጥ የሚገኙ 7 ህንፃዎች ታሪካዊ ይዞታቸውን እንደጠበቁ የሚታደሱ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡ ይሁንና አስተዳደሩ ይህን ባለ ማግስት የአራዳ ክፍለ ከተማ በሁለት ቀናት ውስጥ እቃችሁን ካላወጣችሁ ቤቶቹን በላያችሁ ላይ እናፈርሳቸዋለን ሲል ማስጠንቀቂያ ሰጥቶናል ይላሉ፤ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስር ያሉ የንግድ ተቋማት፡፡ አንበሳ መድሃኒት ቤትና ኒዬን አዲስን ጨምሮ በፕሮጀክቱ […]

በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ስምንት ዝሆኖች በህገወጥ አዳኞች ተገደሉ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል በሚገኘው በማጎ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በህገ-ወጥ ታጣቂዎች ባሳለፍነው ሳምንት አምስት ዝሆኖች ሲገደሉ ሶስት የሚደርሱ ሌሎች ዝሆኖች ደግሞ መቁሰላችወን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይሁንና ትናንት በተደረገ አሰሳ ቆስለው የነበሩ ተጨማሪ ሶስት ዝሆኖች እንደሞቱ ማረጋገጣቸውን የፓርኩ ዋርደን አቶ ጋናቡል ቡልሚ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ከተገደሉት ዝሆኖች መካከል ሴት ዝሆኖች እንዳሉበት የነገሩን የፓርኩ ዋርደን እነዚህ ህገወጥ የዱር እንስሳት […]

የትግራይ ክልል አምስት መገናኛ ብዙሃንን ሐሰተኛ ዘገባዎችን ዘግበዋል በሚል ከሰሰ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሰልጣን በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው አራት የፌደራል መንግስት ንብረት የሆኑ እና አንድ የክልል መገናኛ ብዙሃንን ከሷል። ተከሳሽ መገናኛ ብዙሃኖቹም የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ የኣማራ መገናኛ ብዙሃን ናቸው። እነዚህ መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል ያልተፈጠረ ነገር በሀሰት ዘገባዎችን እየሰሩ በመሆኑ ባለስልጣኑ ጉዳዩን መርምሮ […]

በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተመዘገበዉ ሞት ስምንት ደረሰ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በተጓደኝ ህመም ምክንያት ህክምና ላይ የነበሩ የ62 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ወንድ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኃላ የምርመራዉ ዉጤት ሳይደርስ ህይወታቸዉ አልፏል።በምርመራዉ ዉጤቱ ቫይረሱ እንዳለባቸዉ ተረጋግጧል፡፡ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 137 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 968 ደርሷል፡፡ የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡- ~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ5015 […]

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5015 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት (137) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በተጓዳኝ ህመም ህክምና ላይ የነበሩ የ62 አመት ወንድ የምርመራ ናሙና ተወስዶ ውጤቱ ሳይታወቅ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ቫይረሱ እንደነበረባቸው የተገለጸ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 8 የደረሰ ሲሆን ተጨማሪ 4 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህመም ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት (968) ደርሷል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያንግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 76 ቢሊዮን ብር በብድር እና በእርዳታ ማግኘቷን የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚንስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2012 በጀት ዓመት የ 9 ወራት ከውጭ የተገኙ ብድርና እርዳታ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ሚኒሰትሩ እንዳሉት በ2ዐ12 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከሁለቱም ምንጮች በብድር ብር 42.31 ቢሊዮን የተገኘ ሲሆን በእርዳታ ብር 32.788 ቢሊዮን ተገኝቷል፡፡ በድምሩ ብር 76 ቢሊዮን ብር ፍሰት ተመዝግቧል ተብሏል፡፡ ድጋፉ እና ብደሩም […]

የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር ለኤካ ኮተቤ እና ለጳውሎስ ሆስፒታሎች ከ800 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ የገዛቸውን የህክምና ቁሳቁስ እና ታብሌቶችን ድጋፍ አደረገ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ከ800 በላይ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በአባልነት የያዘው የአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር (ኢትዮጵያ) ከተመሠረተበት 1965 ዓም ጀምሮ ስለበረራ ደህንነት እንዲሁም ስለአብራሪዎች ሙያዊ ብቃት አና መብት ላይ እየሰራ ያለ ሙያዊ ማህበር ነው። ማህበሩ በአሁን ሰዓት በአለም ላይ በፍጥነት አና በአስከፊ ሁኔታ እየተዛመተ የመጣውን የCOVID-19 ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን አገራዊ ዝግጅትና ርብርብ ለማገዝ፣ ከአየር መንገድ አውሮፕላን አብራሪዎች ማህበር አባላት […]

በኢትዮጵያ ከመቶ እናቶች ውስጥ በወር አበባ ጉዳይ ከሴት ልጆቻው ጋር የሚወያዩት ሁለቱ ብቻ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ሚኒስቴርና ዩኒሴፍ በጋራ ያወጡት ሪፖርት እንደሚሳየው በኢትዮጵያ ከመቶ እናቶች መካከል ከሴት ልጃቸው ጋር በወር አበባ ጉዳይ የሚወያዩት ሁለቱ ብቻ ናቸው ተብሏል።ሴት ልጆቻቸው የወር አበባ ከማየቷ በፊት በጉዳዩ ላይ የሚወያዩት ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ ከ10 ሴት ተማሪዎች ደግሞ ከአንድ በላይ የሚሆኑት በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት ቤት ይቀራሉ ፡፡ በተጨማሪ ከ3 ሴት ተማሪዎች አንዷ የተጠቀመችበትን የወር አበባ […]

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ከ950 በላይ ሰዎች ድንገተኛ አደጋዎች ደርሶባቸዋል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአቤት ሆስፒታል የቃጠሎ እና ድንገተኛ ህክምና ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው በመጋቢት ወር ብቻ 23 ሰዎች በድንገተኛ አደጋ ሕወታቸው አልፏል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ምክንያት የእንቅስቃሴ ገደብ ቢጣልም ጎን ለጎን የድንገተኛ አደጋዎች የመከላከል ስራ ትኩረት እንደተነፈገውም ተገልጿል። በአቤት የቃጠሎ እና ድንገተኛ ህክምና ሆስፒታል በመጋቢት እና በሚያዚያ ወር ብቻ ከ950 በላይ ሰዎች ድገተኛ አደጋ ደርሶባቸዋል።ከዚህ አደጋ ውስጥም […]

ኮቪድ19 ሆፕ ፎር አፍሪካ ኮንሰርት የተሰኘ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ ድግስ የፊታችን እሁድ ምሽት ይካሄዳል ተባለ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

መልቲቾይዝ ኢትዮጵያ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ይህ ኮንሰርት መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ታላላቅ የአፍሪካ አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ይሳተፋሉ ብሏል። ኮንሰርቱ መልቲቾይስ ከዋን አፍሪካ ግሎባል ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ ቻናል 154 የፊታችን እሁድ ግንቦት 23/2012 ከምሽቱ 2 ሰአት ጀምሮ ይተላለፋል ተብሏል። ይህ ኮንሰርት በመላው አፍሪካ በዲኤስቲቪ Africa Magic […]