ብሔራዊ ሎተሪ በየ አስራ አምስት ቀኑ ያወጣ የነበረውን የመደበኛ ሎተሪ እጣ አቋረጠ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር 600 ሺህ ብር ደርሶ የነበረው የመደበኛ ሎተሪ እጣ አስተዳደሩ በደረሰበት ኪሳራ ምክንያት እጣው እንዲቋረጥ መወሰኑን ገልጿል፡፡ የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ የመደበኛ ሎተሪ የሎተሪ ሺያጭ በ30 በመቶ እንደቀነሰበትም ነው አስተዳደሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም የተናገረው፡፡ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ ንዋይ እንደተናገሩት ባጭር ጊዜ ሎተሪው ተሸጦ ካላለቀ ከፍተኛ ኪሳራ ነው […]

ዜና እረፍት

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በድምፃዊነት በዜማና ግጥም ስራው ትልቅ አሻራ ያኖረውና እርሱም በማቀንቀን የሚታወቀው ሱራፌል አበበ ዛሬ ከዚህ አለም ተለይቷል። የተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አባት የሆነው ሱራፌል አበበ ቀብርና ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እንገልጻለን።ኢትዮ ኤፍ ኤም ለቤተሰቡ ና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል። #ምንጭ አቻሬ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4809 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አስራ ስድስት (116) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4070 ደርሷል። ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 37 (24 ከጤና ተቋም እና 13 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከጤና ተቋም እና አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በተጨማሪ አምስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው […]

ለአስዋን ግድብ ውሀ የሚያቀርብ ግድብ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊሰራ ታቅዶ እንደነበር ያውቁ ኖሯል?

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

እንግሊዝ ግብፅ ውስጥ በስፋት ጥጥ ታመርት ነበር፤ ያ ጥጥ ወደ እንግሊዝ ሄዶ የሱፍ ጨርቅ ይመረትበት ስለነበር፤ የአባይ ውሀ ፍሰት እንዳይቀንስ ትሰጋ ነበር፡፡ በአሜሪካን ሀገር መኖርያቸውን ያደረጉት የምህንድስና ባለሙያው እና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ጥናቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ የሚታወቁት አቶ ሲሳይ አለማየሁ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ባደረጉት ቆይታ የግብጽ ፍላጎት ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን በድህነት ውስጥ ስትዳክር […]

ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር እና የገጠመው የኮሮና ቫይረስ ፈተና

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር ባሳለፍነው ረቡዕ 10 ቀን 2012 ዓ.ም የተለመደውን በጎ ተግባሩን በማከናወን ላይ ሳለ ያልጠበቀው ክስተት እንደተፈጠረ አጋርቶናል፡፡ የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ መለሰ አየለ እንደነገሩን በእለቱ አየር ጤና ሀና ማርያም አካባቢ አንድ የአእምሮ ህመምተኛ ከጎዳና አንስተው ከሽሮሜዳ ከፍ ብሎ ቁስቋም 17 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ ወደሚገኘው የማህበሩ ጊቢ ለመውሰድ መንገድ ይጀምራሉ፡፡ ታማሚውንም ወደ […]

ኢትዮጵያ ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት ለኮቪድ-19 ህሙማን ለመጠቀም ወሰነች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የጤና ጥበቃ ሚኒስተር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት “ለኮቪድ-19 ህሙማን የሚውለውን ዴክሳሜታዞን የተባለውን መድሀኒት በተመለከተ በእንግሊዝ መንግስት የተካሄደውን ጥናት እና ሪፖርት በዝርዝር ተመልክተነዋል፡፡” የህክምና ጉዳዮች አማካሪ ቡድናችን እና የጤና ባለሙያዎች አማካሪ ምክር ቤት፣ የሰጠንን ምክረ ሀሳብ መሰረት በማድረግ፣ ኦክሲጅን ወይም የመተንፈሻ መሳሪያ እገዛ ለሚያስፈልጋቸው የኮቪድ-19 ህሙማን አነስተኛ መጠን ያለው ዴክሳሜታዞን እንደ ድኝገተኛ ህክምና ለመጠቀም ተወስኗል” ብለዋል። […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 195 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ተጨማሪ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,853 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠና አምስት (195) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አራት (3,954) ደርሷል፡፡ በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አምስት (85) ሰዎች (73 ከአዲስ አበባ እና 5 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአማራ ክልል እና 2 ከትግራይ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ […]

ባለፉት አምሰት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ የወጣላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር ተያዙ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ (ከሰኔ 6-10/12 ዓ.ም) ብቻ ግምታዊ ዋጋቸው ከ16 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ንግድ ማጭበርበር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡በሁሉም የሀገርቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎችና ኬላዎች ላይ በተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የኮንትሮባንድና የንግድ ማጭበርበር እንቅስቃሴዎችን የመቆጣጠር እና የማጋለጥ ስራ ተጠናክሮ ቀጥለዋል። ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል የተለያዩ ዓይነት አዳዲስና አሮጌ አልባሳት፣ የአዋቂና የህፃናት ጫማዎች፣ […]

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን የአገሪቱ 10ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ የሥልጣን ርክክብ ለማድረግ የቀረበውን አጀንዳ ተቀብሎ አጸደቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ አጀንዳውን ያጸደቀው ከደቂቃዎች በፊት በሀዋሳ ከተማ በጀመረው የምክር ቤቱ አምስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤው ነው ። በጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱን የመወያያ አጀንዳዎች ያቀረቡት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ምክር ቤቱ በዚህ ጉባኤ ከሚመለከታቸው አጀንዳዎቹ መካከል አንዱ የሲዳማ ዞን የሥልጣን ርክክብ መሆኑን ለጉባኤው አባላት ገልጸዋል። አሁን ለጉባኤው የቀረበው አጀንዳ የሲዳማ […]

የገቢዎች ሚኒስቴር አምስተኛ የግብር መክፈያ ቅርንጫፍን በአዲስ አበባ ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የሚገኙ 24 ሺህ 900 የፌደራል ግብር ከፋዮችን እንደ አዲስ በአምስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይደራጃሉ ተብሏል፡፡ በአራት ቅርንጫፎቹ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሀምሌ 1 ጀምሮ አምስተኛውን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሊከፍት መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ቀደም ሲል ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት፣ የምስራቅና ምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም […]