ቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ የኮሮና ቫይረስ ስጋት አለመሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ ከዘጠኝ ወራት እስከ አንድ ዓመት ባሉት ጊዜ ውስጥ እንዲካሄድ ተወሰነ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በሃገሪቱ ስጋት ሆኖ እስከቀጠለ ድረስ ሁሉም የፌደራልና ክልል ምክር ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ በሚል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አጽድቋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ እያካሄደ ነው። የምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን ከማራዘም ጋር በተያያዘ የቀረበለትን የህገ መንግስት […]

የሕዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ሁለተኛ ቀን ውይይት ከሰዓታት በኋላ ይጀመራል

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ድርድሩ የደቡብ አፍሪካ፣አውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ታዛቢዎች በተገኙበት እንደሚከሄድ ተገልጿል። የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሙሌት እና ዓመታዊ የውሃ አለቃቅ በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ድርድር ትናንት ተካሂዷል። ድርድሩ በበይነ-መረብ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ታዛቢዎች በተገኙበት በውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ተካሂዷል። በዚህ ድርድር ላይ በደቡብ […]

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ብስለት ከጎደለው መግለጫው እንዲታቀብ ኦነግ አሳሰበ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፈው ሳምንት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ”ሕዝቡ ከአገር ጥቅም በተቃራኒ ከቆሙት አካላት ሊጠነቀቅ ይገባል” ሲል በሰጠው መግለጫ በግብፅ የሚደገፍ ቡድንና ወያኔ ከሀገር ጥቅም በተቃራኒ የቆሙ ናቸው ማለቱ ይታወሳል፡፡ በክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ሶስተኛውከሀገር ጥቅም በተቃራኒ የቆሙት ቡድኖች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ናቸው ያሉ ሲሆን ምርጫ መራዘሙን መነሻ ምክንያት […]

የግል ሆስፒታሎች እና ክሊኒኮች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት በመዘጋት ላይ መሆናቸውን ተገለፀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጲያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው፤ ህብረተሰቡ በዚህ ሰእት ለመደበኛ የህክምና አግልግሎት ወደ ጤና ተቋማት የመሄድ ልምዱ ቀንሷል። በዚህም ምክንያት ተቋማቱ አግልግሎት እየሰጡ አይደለም። ከሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ የህክምና ግብአት አቅራቢዎችም ከገበያ ውጪ እየሆኑ በመምጣታቸው ለህንፃ ኪራይና ለሰራተኛ ደሞዝ ለመክፈል ተቸግረዋል ነው የተባለው። በመሆኑም በርካቶቹ ተቋማት እንደሚዘጉ ማህበራችን ያውቃል ብለዋል፤ የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት ዶ/ር […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 190ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 190 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ የ 5 ሰዎች ህይወት ደግሞ ማለፉ ተገልጿል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,995 የላብራቶሪ ምርመራ 190ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,336 መድረሱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ 5 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው […]

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ግንቦት 23/2012 ዓ.ም ህግ በማስከበር ላይ የነበሩ የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የወረዳው የህዝብ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ በነበሩት አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅመው መሰወራቸውን ይታወቃል። ሆኖም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ከነዋሪዎች ጋር ተቀናጅተው በመስራት 01/10/2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ አስታውቋል። ወንጀሉ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ ኃይሉና የአካባቢው ማህበረሰብ ተጠርጣሪዎች […]

ኢትዮጵያ በሚያዚያ ወር ወጪ ንግድ 329 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በ2012 በጀት ዓመት በሚያዚያ ወር ከግብርና ፣ ከማኑፋክቸሪንግ ፣ ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ እና ከሌሎች ምርቶች 365.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር። አፈጻጸሙም 329 ነጥብ 3 ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን የእቅዱን 90 በመቶ መሳካቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ከተገኘው 249 […]

ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በ2012 በጀት ዓመት አስር ወራት ከወጪ ንግድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል። ይህ አፈፃፀም በ2011 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ271 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ አለው። በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት […]

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የትግራይ ክልል ኮሙንኬሽን በማህበራዊ ድረገጹ እንዳስታወቀው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሆኑት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነታው ለቀዋል። ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ሚያዝያ 2010 ዓ.ም ነበር የፌዴራሽን ምክር ቤት ተደርገው መሾማቸው ይታወሳል። ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8 ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያንሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 136 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,775 የላብራቶሪ ምርመራ 136 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2,156 ደርሷል። እንዲሁም 17 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ የገገሙ ሰዎች 361 ደርሷል። ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8 ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያንሰኔ 1 ቀን […]