በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,352 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ (731) ደርሷል፡፡ የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦ • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 11 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 5 […]

በጋምቤላ ክልል ኮሮና ቫይረስ መመርመር ተጀመረ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ይህ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማዕከል በቀን 180 የኮሮና ቫይረስ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚያስችል የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ በክልሉ ምርመራ መጀመሩ ጊዜንና ወጪን ከመቆጠብ በተጨማሪ በክልሉ በተለያዩ ለይቶ ማቆያዎች ለሚገኙ ዜጎች በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተመልክቷል፡፡ ከደቡብ ሱዳን በሚገቡ ስደተኞች ከፍተኛ የኮሮና ስጋት ያለበት የጋምቤላ ክልል ኮሮና ቫይረስን መመርመር የሚያስችል የምርመራ ጣቢያ ዛሬ የክልሉ አመራሮች ስራ አስጀምረዋል። […]

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬት ወስደው በሚገባ ያላለሙ 20 ኢንቨስተሮችን መሬት መቀማቱን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ የአካባቢ መሬት አስተዳደርና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታ ሃይሉ እንዳሉት በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶችን የስራ እንቅስቃሴ በመገምገም የወሰዱትን መሬት ሳያለሙ በተገኙ 18 የእርሻና 2 በእጣን ማምረት የተሰማሩ የኢንቨስትመንት ባለሃብቶች ፈቃድና የመሬት ውላቸው ተሰርዟል። በክልሉ 103 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበው ውል በመግባት 8 ሺህ 376 ሄክታር መሬት በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፉ ተሰማርተዋል። ይሁንና እነዚህ […]

የትግራይ ሕዝብ ለነጻነት እና እኩልነት የሚያደርገውን ትግል እንደሚደግፍ አብን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የትግራይ ሕዝብ ለነጻነት እና እኩልነት የሚያደርገውን ትግል እንደሚደግፍ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የትግራይና የአማራ ሕዝብ ለዘመናት የዘለቀ ወዳጅነት አላቸው ህዝቦች ናቸው ያለው አብን “ትሕነግ” ባለው በህወሓት ሲራመድ በነበረው ስርዓት ምክንያት የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ፈተና ላይ ወድቆ ቆይቷል ብሏል። ሕወኃት በአገራችን በልዩ ሁኔታ ደግሞ በአማራ ሕዝብ ላይ በጥላቻ ተመስርቶ ሥራ ላይ ባዋለው […]

በአዲስ አበባ አራት የግል ትምህርት ቤቶች ለአንድ ዓመት ታገዱ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዛሬ በሰጠው መግለጫ በአዲስ አበባ አራት ትምህርት ቤቶች በቀጠቀዩ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳያስተምሩ ታግደዋል። ባለሰልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤት ክፍያቸውን ከ50 እስከ 75 በመቶ እንዲቀንሱ መመሪያ ቢያስተላልፍም ትምህርት ቤቶቹ ግን 100 ፐርሰነት ክፍያ አስከፍለው ነው። ለአንድ ዓመት ከታገዱት ትምህርት […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 46 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ተጨማሪ የአንድ ሰው ሞት መመዝገቡን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ አንድ (701) ደርሷል፡፡ የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦ • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 34 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 4 […]

በአዲስ አበባ ቦሌ አትላስ አካባቢ ዛሬ ሌሊት በአንድ መኖሪያ ቤት በጦር መሳሪያ እና በኤሌክትሪክ ሾክ የታገዘ ዝርፊያ ተፈጸመ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከኡራኤል ቦሌ አትላስ መስመር አካባቢ በተለምዶ ይልማ ስጋ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ማለትም ሰኞ ለማክሰኞ ሌሊት ላይ የተደራጁ ዘራፊዎች በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ዝርፊያ መፈጸማቸው ተገልጿል። ዝርፊያው የተፈጸመበት ግለሰብ አቶ ረብራ ተሸመ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳለው ዘራፊዎቹ በጦር መሳሪያ እና የኤሌክትሪክ ሾክ በመጠቀም 2 ላፕ ቶፕ 2 አይፎን ስልኮች 10 ሺህ 800 […]

በትግራይ እየተካሄደ ያለው የወጣቶች አመጽ የህወሃት አመራሮች የጥቅም ሰንሰለት የፈጠረው ችግር መሆኑን አረና አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ እየተካሄደ ያለው ይሄንን አመጽ ፓርቲው እንደሚደግፈውም አስታውቋል። የኮሮና ቫይረስ መከሰት በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የማስከተሉን ያክል የፖለቲካውን አለም መልክም በከፊል ቀይሮት ቆይቷል፡፡ ሃገራችን በተለያዩ ጎራዎች በተሰለፉ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች እየተናጠች በነበረችበት ቅድመ- ኮሮና ዘመን ፤ በአንጻራዊነት ሰላም የሰፈነባት ክልል ነበረች፤ትግራይ፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ክልሉን የሚመራው ፓርቲ አምባገነንነት ነው የሚለውን መከራከሪያ የሚያነሱ በርካቶች ናቸው። ከሰሞኑ ታዲያ በእለታዊው […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 73 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,844 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሶስት (73) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት (655) ደርሷል፡፡የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦ • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 27 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 15 […]