ልጁን በመስሪያ ቢሮው ስም የሰየመው ኢንዶኔዢያዊ አነጋጋሪ ሆኗል

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ሳሜት ዋህዩዲ ይባላል ስራውንና ስራ ቦታውን በጣም ከመውደዱ የተነሳ የስራ ክፍሉን ስም ወስዶ የልጁ መጠርያ አድርጎታል፡፡ በአሁን ሰአት የዚህ የ 5 ወር ህፃን ልጅ ስምና አባቱ የሚሰራበት የስራ ክፍል ስም ተመሳሳይ የሆነ ሲሆን ፤ስታትስቲካዊ መረጃዎች ተግባቦት ቢሮ፤ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ገና ከማግባቱ በፊት ነው ሳሜት ልጅ ስወልድ ልጄን በስራ ክፍሌ ስም ነው የምጠራው ሲል ለራሱን ቃል […]

ኬንያ ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ አቋረጠች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ወደአለባት ወደ ሕንድ የምታደርገዉን የመንገደኞች በረራ ላልተወሰነ ጊዜ ማቋጧን አሳወቃለች፡፡ ውሳኔው የጭነት በረራዎችን አይመለከትም ተብሏል እንደ ዴይሊ ኔሽን ዘገባ፡፡ እስካሁን እንደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንግሊዝ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት ወደ ሕንድ የሚደርጉትን በረራ አቋርጠዋል፡፡ ኬንያ በሚቀጥሉት 72 ሰዓታት ውስጥ ከሕንድ ወደ ኬንያ የሚመጡ መንገደኞችን በለይቶ ማቆያ ቦታ እንዲገቡ […]

ራማፎሳ ኤኤንሲ (ANC) ሙስናን ለማስቆም አለመቻሉን አምነዋል

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ አገዛዝ ወቅት ገዥው ፓርቲ ሙስናን ለመከላከል አለመቻሉን አምነዋል፡፡ ዙማ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት በሙስና የተጠረጠሩ ክሶችን ለመመርመርና ፍትህ ለማሰጠት በቂ ስራ አልሰራም ብለዋል፡፡ ኤ.ኤን.ሲ ተጠያቂነትን ለማስፈፀም የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ የሚጠብቀውን ያህል እንዳልሰራ በመግለጽ ሙስና የህግ የበላይነት እንዳይረጋገጥ አድርጓል ብለዋል፡፡ “ስልጣንን እና የመንግስትን ሀብቶችን […]

ቱርክ እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ ለመገደብ መዘጋጀቷን አስታወቀች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለዉ የቱርክ መንግስት፣ ስርጭቱን ለመግታት ለጊዜዉ እንቅስቃሴን መገደብ የተሻለዉ አማራጭ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብሏል፡፡ ይህን ተከትሎ በኢስታንቡል የሚገኙ የግብይት ማዕከላት በሸማቾች ተጨናንቀዋል፡፡ ቀደም ሲል በአዉሮፓ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በእጅጉ በተስፋፋበት ወቅት፣ ቱርክ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ዉጤታማ ስራ ሰርታለች በሚል በዓለም ጤና ድርጅት ስትወደስ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በአሁኑ ወቅት […]

የአውሮፓ ህብረት አስትራዜኒካን ከሰሰ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የአውሮፓ ህብረት ሰኞ ዕለት በሕክምናው መስክ ግዙፍ በሆነው አስትራዜኔካ ላይ በኮሮና ቫይረስ ክትባት አቅርቦትን በማዘግየቱ በአህጉራችን አውሮፓ ለማስጀመር ያቀድነውን ጥረት አደናቅፎብናል በማለት መክሰሱን ተሰምቷል ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ እስቴፋን ዴ ኬርስማየር እንዳሉት ኮሚሽኑ ባለፈው አርብ በተሻሻለው የግዢ ስምምነት ጥሰት ላይ በመመስረት ኩባንያው አስትራዜኔካ ላይ ክስ መመስረታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው ክትባቱን በወቅቱ ማድረሱን የሚያረጋግጥ አስተማማኝ ስትራቴጂ […]

ጋምቢያ ትራኮማን ሙሉ በሙሉ በማጣፋት ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

አይነ ስውርነትን የሚያስከትለውን ትራኮማን ከሀገሯ በማስወገድ ጋምቢያ ከአፍሪካ ሁለተኛዋ ሀገር መሆኗን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንዳመለከተዉ በዓለም ላይ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች በዚህ ህመም ተጠቅተዋል፡፡ የጋምቢያ መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች በርካታ አመታት ቤት ለቤት በመዞር በተለይ በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍል ህሙማንን የማከም ስራ መስራታቸውም በዘገባው ተካቷል፡፡ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ በንክኪ እንደሚሰራጭ የሚነገረው […]

የአውሮፓ ህብረት ለደቡብ ሱዳን 51 ሚሊየን ዶላር መመደቡን አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ደቡብ ሱዳን ያለችበትን የርሀብ ወቅት እንድትቋቋም 51 ሚሊየን ዶላር መድቤያለው ሲል የአውሮፓ ህብረት ሲል አስታውቋል፡፡ ህብረቱ የመደበው ገንዘብ ለምግብ ፍጆታ፣ለሰው ሰራሽና ለተፈጥሮ አደጋዎች መቋቋሚያ እንደሚውል ተነግሯል፡፡ በደቡብ ሱዳን ያለው የሰዎች ሁኔታ እጅግ አስከፊ እንደሆነ የጠቆመዉ ዘገባዉ፣ጉዳዩ አሳሳቢና ትኩረት የሚሻው እንደመሆኑ በቂ የሆነ አለምአቀፋዊ ትኩረት አላገኘም ብሏል፡፡ እስካሁን ለደቡብ ሱዳን እጃቸውን የዘረጉት የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ 5 […]

አንዳንድ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተሰጣቸውን የአየር ሰዓት በትክክል መጠቀም አልቻሉም ተባለ።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8ን ጨምሮ በሃገሪቱ በሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ለ 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ተፎካካሪ የሆኑ የፓለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ ቅስቀሳ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ድልድል መሰረት በየመገናኛ ብዙሃኑ የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ። ይሁንና ኢትዩ ኤፍ ኤምን ጨምሮ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎቹ፣ ቅስቀሳቸውን በሚያካሂዱባቸው መገናኛ ብዙሃኖች ላይ፣ የተሰጣቸውን የአየር ሰዓት በተገቢው እየተጠቀሙበት እንዳልሆነ መገናኛ ብዙሃኑ […]

በሊቢያ የነዳጅ ዘይት ወደቦች ላይ ጉዳት እያጋጠመ መሆኑ ተነገረ።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የሊቢያ ብሔራዊ የነዳጅ ዘይት ኮርፖሬሽን እንዳለው በዋና ዋና የነዳጅ ወደቦች ላይ የሃይል መቆራረጥ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እየተከሰተ ነው ብሏል። በመንግስት የሚተዳደረው የሊቢያ የነዳጅ ዘይት ኮርፖሬሽን (NOC) እንዳስታወቀው፣ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ትላልቅ የነዳጅ ወደቦች አንዷ በሆነችው በሃሪጋ ወደብ ላይ የኃይል አቅርቦት ጉዳት መከሰቱን አስታውቋል፡፡ የሊቢያ ማዕከላዊ ባንክም የነዳጅ ዘይቱ በሚገኙባቸው ወደቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለማካካስ […]

ዴሪክ ቾቪን በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተባለ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ዴሪክ ቾቢን ባለፈው ዓመት በሚኒሶታ ጎዳና ላይ አፍሪካ አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍሎይድን ትከሻው ላይ በመጫን ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን ተከትሎ በዓለም ላይ በጥቁሮች ላይ የሚታየውን ዘረኝነት የሚያወግዝ ታላቅ የእንቅስቃሴ ተቃውሞ ተካሂዷል፡፡ ለዚህ ንቅናቄ ዘመቻ ምክንያት የሆነው የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ተጠያቂው ዴሪክ ቾቢን የተሰኘው የሚኒያ ፓሊስ ለህግ እንዲቀርብ በርካቶች ጩኃታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ ለዘህ ፍርድ የተሰኘመው ዳኛም ዴሪክ ቾቪን […]