ስለ ኢትዮ ኤፍ ኤም

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በንግዳችን ፍሬያማነት ውስጥ የድርሻውን ኃላፊነት የሚወስድ፣ የህይወት ዳገቶች እንዲለዝቡ በርትቶ የሚሰራ፣ ኑሮአችንን የሚኗኑረን፣ በትኩስ መረጃዎች የሚያደረጀን፣ ለመዝናናት ፍላጎታችን በቂ መልስ ያለው፣ በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ የሚተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብን የሚያስቀድም ነው የእርስዎ ሬዲዮ ጣቢያ፡፡

“ሁሉም ሸማች፣ ሁሉም ሻጭ ነው፤ መገበያያው አይነቱ በርካታ ይሁን እንጂ በህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ ይመሰረታል” በሚል ተቀዳሚ መነሻ፣ ይህ በሰዎች ወይም ተቋማት መካከል የሚኖር የመረጃ፣ የሀሳብ፣ የእሴት፣ የቁሳቁስ፣ የአገልግሎት፣ … ቅብብሎሽ በዕውቀት፣ በፍትሃዊነት፣ በሠብዓዊነት፣ በዘለቄታዊነት፣ በመተሳሰብና መከባበር፣ … ላይ እንዲመሰረት ከህዝቡም፣ ከመንግስትም፣ ከሊቃውንትም፣ ከሃይማኖት መሪዎችም፣ ከባለሙያዎችም … ጋር እየሰራ፣ ራሱን በስትራቴጂ፣ በዕቅድ፣ በመሰረተ ልማት፣ በሰው ኃይል፣ በሲስተም እያበለፀገ ከመሃል ቦሌ የቀጥታ መደበኛ ስርጭት እነሆ ያለ ጣቢያ፡፡

ሬዲዮ ጣቢያዎ ያለማቋረጥ፣ ለተከታታይ 18 ሠዓታት አየር ላይ ለመቆየት የሚያስችል ቴክኒካዊ ብቃት ገንብቷል፤ አዲስ አበባን ጨምሮ እሰከ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ አዳማ፣ ፍቼ፣ መተሃራ፣ ዝዋይ፣ ደብረብርሃን፣ ስልጤ ዞን፣ … ስርጭቱ በሚደረስበት አካባቢዎች ሁሉ በሚሊዮኖች፣ በጣም በስፋትና በከፍታ እየተደመጠ መገኘቱ አንድም በፕሮግራሞቹ አንድም በሞገዱ በሚፈሰው ድምፅ ጥራት ስለመሆኑ የአድምጮቹ ምስክርነት ዋቢ ነው፡፡

ዲጂታል ቴክኖሎጂው የፈጠረውን ዕድል በመጠቀም ዘመኑን ለመዋጀት ራሱን የቻለ የዲጂታል ሬዲዮ የስራ ክፍል ተፈጥሮ ከ107.8 የአየር ሞገድ በተጨማሪ በስልክ መተግበሪያ /App/፣ በፌስቡክ፣ በድረገጽ፣ በቴሌግራም፣ በዩቲዩብ … ሬዲዮ ጣቢያዎ የማይረግጥበት የዓለማችን ጠርዝ የለም፡፡

በቀን ውስጥ ማለዳና ምሳ ሠዓት ላይ የሚቀርቡ በጣቢያው ጋዜጠኞች የሚዘጋጁ እና ዘወትር ከምሽቱ 1፡00-2፡00 ከጀርመን ድምፅ በቀጥታ የሚተላለፉት  ዜናዎች፣  ከሠላሳ በላይ በሬዲዮ ጣቢያው እና በተባባሪ አዘጋጆች ተዘጋጅተው የሚቀርቡ መረጃ ሰጪ፣ አዝናኝ፣ አሳዋቂ እና የስፖርት ፕሮግራሞች በዘርፉ ያለውን ክፍተት ታሳቢ ያደረጉና በአዲስ መልክ የተቃኙ ናቸው፡፡ ሙዚቃ እንደ ማጀቢያ ሳይሆን የኢትዮ ኤፍኤም 107.8 አንዱ መሰረታዊ ይዘት ተደርጎ ስትራቴጂው መነደፉ ጣቢያችን የ“ኤፍኤም ሬዲዮ” መፈልሰፍን ዋነኛ ምክንያት ያለመዘንጋቱን ማሳያና ከአድማጩም ጥያቄ ጋር የሚጣጣም ነው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

የኢትዮጵያዊያን