በዓልን ምክንያት በማድረግ የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ተነግሯል

የትንሳዔ በዓልን አስመልክቶ 188 የእሁድ ገበያዎች ሳምንቱን ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስውቋል፡፡

በዓልን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በመዲናዋ የሚገኙ 188 የእሁድ ገበያዎች በመደበኛነት ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደውን የእሁድ ገበያዎች፤ ሳምንቱን ሙሉ እንዲካሄዱ መደረጉን የቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡

ይህም በዓልን አስመልክቶ የሚፈጠር የምርት እጥረት፣ ህገ ወጥ ንግድን እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡

የእሁድ ገበያዎቹ የትራስፖርት አገልግሎት ላይ መጨናነቅ የማይፈጥሩት ተለይተው መሆኑን አንስተው፤ በእነዚህ የገበያ ቦታዎች ላይ የገበያ ዋጋ ጥናት በቢሮ በየ 3 ቀኑ የሚከናወን እና የዋጋ ተመን እንደሚዘጋጅ እና የክትትል ስራ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡

እሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *