የፈረንጆቹ አዲሱ አመት 2021 ከገባ ወዲህ 43 አፍሪካውያን ስደተኞች በሜዲትራንያን ባህር መሞታቸው ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አዲሱ አመት ከገባ በ21 ቀናት ውስጥ ብቻ፤ በሊቢያ አድርገው ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባታ በሚሞክሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ውስጥ፤ 43 የሚሆኑት የሚሄዱበት ጀልባ ተገልብጦ መሞታቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል። ያሳለፍነው ማክሰኞም ቢሆን ከሊቢያ ወደብ ከተማ ዛውያ ተነስቶ ስደተኞችን ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ጀልባ በሜዲትራንያን በህር ላይ ትንሽ ርቀቶችን እንደተጓዘ መገልበጡንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡ ስደተኞቹ […]

ውቅሮ ፣አዲግራት እና ደገ ሀሙስ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት በትግራይ ክልል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር ጥረቶች ቀጥለዋል ብለዋል። በአዲግራት፣ውቅሮ እና እደጋ ሀሙስ አካባቢዎች ኔትወርክ አገልግሎት ተጀምሯል ብለዋል። በሌሎች አካባቢዎችንም የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር የጥገና ስራዎችን እየሰራን ነውም ብለዋል። የሳይበር ጥቃት ሙከራ በስራችን ላይ ችግር ሆኖብን ነበር ነገር ግን ኔትዎርካችን ሳይነካ መክተን አልፈናል ሲሉም ስራ አስፈጻሚዋ […]

ቻይና በ28 የአሜሪካ ሰዎች ላይ ማእቀብ ጣለች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ቻይና ማይክ ፖምፒዮን ጨምሮ በ28 በቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣኖች ላይ ማእቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡ ሀገሪቷ በቀድሞ የአሜሪካ ባለስልጣኖች ላይ ማእቀቡን የጣለችው በቻይኛ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል እንደሆነ አልጀዚራ ዘግቧል። ማእቀቡ ከተጣለባቸው የቀድሞ ባለስልጣናት መካከል የትራምፕ የንግድ ጉዳዮች አማካሪ የነበሩት ፒተር ናቫሮ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሮበርት ኦብሪን በተባበሩት ምንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ተወካይ ኬሊ ክራፍት እና ሌሎችም […]

በትግራይ 92 የምግብ ማሰራጫ ማዕከላት መቋቋሙ ተገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል። በትግራይ ህግ ከማሰከበር ዘመቻ በፊት 1.8 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ የሚፈልጉ ነበሩ። የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና በቤንሻጉል ጉምዝ መተከል ዞን በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ለዜጎች ለማድረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ እና አጠቃላይ በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ነው። […]

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት ከ25 ቢሊየን በላይ ብር ማግኘቱን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በተቋሙ ግማሽ ዓመት አፈጸጸም ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው። ወይዘሪት ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል። ገቢው ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጸጸር በ12.3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ተቋሙ በአጠቃላይ 50.7 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት ተገልጿል። ካሉት ደንበኞች ውስጥ 48.9 ሚሊዮኖቹ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ […]

የፅንፈኛው ህወሓት ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ::

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴል ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የአገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ። የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የፅንፈኛው ህወሓትን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው። መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት […]

125ኛው የአድዋ በዓል የካቲት የአድዋ ወር በሚል ከየካቲት 1 ቀን ጀምሮ እንደሚከበር የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ሚንስቴሩ በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ከብዙሀን መገናኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው። በዚህ ጊዜ እንደተገለጸው 125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። የአድዋ በዓል በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ አንድነታችንን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ተብሏል። ከበዓሉ አከባበር ዝግጅቶች መካከልም በአገሪቱ ባሉ ሁሉም […]

ኢትዮጵያ ድሮኖችን በአገር ውስጥ ማምረት ልትጀምር መሆኑን አስታወቀች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖኖሊጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የድሮን ቴክኖሎጂ ላይ ለመስራት ድሮኖችን ለማምረት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር የሽሩን አለማየሁ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አገሪቱ በራሷ አቅም ድሮኖችን ማምረት የሚያስችል ስራዎች ተጀምረዋል ነዉ ያሉት፡፡ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ስራ […]

ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ሲሰናበቱ ጆ ባይደን ደግሞ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ገብተዋል፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ሀገረ አሜሪካንን ላለፉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነጩን ቤተ መንግስት ለተተኪው ፕሬዝዳን ጆ ባይደን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት አሜሪካንን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የተመረጡት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ በዛሬው እለት በይፋ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ በበዓለ ሲመታቸው ላይ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ባራክ ሁሴን ኦባማ፣ ቢል ክሊንተን እንዲሁም ጆርጅ ደበሊው ቡሽ ሲገኙ ዶናልድ ትራምፕ አሻፈረኝ […]

በትግራይ ክልል በተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ የተሳተፈ የውጭ ሀይል አለመኖሩን አምባሳደር ዲና ተናገሩ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ እና የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ የተለያዩ መሆናቸውንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። አምባሳደሩ በመግለጫቸው እንዳሉት ግድቡን በተመለከተ ሱዳኖች ወጣ ገባ አቋም የሚያሳዩቱ በሶስተኛ አካል ምክንያት ነው። የህዳሴው ግድብ ለሱዳን ህዝብ ትልቅ ጥቅም እንደሚያስገኝ ሱዳናዊያን ምሁራን የሚያውቁት ጉዳይ ነው […]