አሜሪካ ለምታሰለጥነው የሱማሊያው ልዩ ኮማንዶ የምትሰጠውን ድጋፍ ልታቋርጥ ነው፡፡

አሜሪካ ለምታሰለጥነው የሱማሊያው ልዩ ኮማንዶ “ዳናብ” የምትሰጠውን የምግብ ድጋፍ ልታቋርጥ መሆኑን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

አሜሪካ የምግብ ድጋፏን ለማቋረጥ የወሰነችው፣ ልዩ ኮማንዶው የምግብና የነዳጅ ድጋፉን መልሶ ገበያ ውስጥ በመሸጥ በሙስና ተዘፍቋል የሚል መረጃ ከደረሳት በኋላ እንደሆነ ዘገባዎቹ ገልጸዋል።

አሜሪካ ለልዩ ኮማንዶው የምታቀርበውን የነዳጅ ድጋፍ ጭምር ልታቋርጥ እንደምትችል ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።

“ዳናብ” ልዩ ኮማንዶ አልሸባብን በመውጋት እውቅናን ያተረፈ የጦር ሠራዊቱ ክፍል ነው።

ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *