ኤልሳልቫዶር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ልትከፍት ነዉ ተባለ

ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፍት መወሰኗን የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታዉቀዋል ተብሏል፡፡

በኤልሳልቫዶር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌክሳንድራ ሂል ቲኖኮ የተመራ ልዑክ ቡድን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች በደቡብ ደቡብ ማዕቀፍ በባለብዙ መድረኮች ትብብራቸውን አጠናክሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ ማድረጋቸዉ ታዉቋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በቀጣይ የፖለቲካ ምክክሮች ለማድረግ በሚያስችሉ እንዲሁም በትምህርት በግብርና በስፖርት እና በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር አጠናክሮ ለመስራት መስማማታቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አባቱ መረቀ
ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *