መጪው የትንሳኤ በዓልን ተከትሎ ባዕድ ነገርን ከምግብ ጋር የሚቀላቅሉ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመቻ ተጀምሯል ተባለ

የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከበዓል  ጋር ተያይዞ በስፋት ለሚከሰተው ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅሎ መሸጥን እና መሰል ድርጊቶችን ለመከላከል ያለመ የቅድመ ጥንቃቄ የዘመቻ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተለይም በበዓላት ወቅት በብዛት አገልግሎት ላይ የሚውሉ እንደ ቅቤ እና በርበሬ መሰል ግብአቶችን ከተለያዩ በአድ ነገሮች ጋር ቀላቅሎ መሸጥ በስፋት የሚስተዋል እንደሆነ ተነስቷል።

የባለሥልጣኑ የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በዓልን ተከትለው የሚያጋጥመውን ምግብን ከተለያዩ ባዕድ ነገሮች ጋር ቀላቅሎ መሸጥ ተግባርን ለመከላከል ያለመ ዘመቻ በከተማችን በስፋት እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ሀላፊዋም እንደሚሉትም  ከኢድ አልፈጥር ጀምሮ ስራዎች እንደተሰሩ አንስተው መጪው የትንሳኤ በአልንም  ተክትለው የሚያጋጥሙ ህገወጥ ተግባራትን ለመከላከል የቅድመ መከላከል ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ነግረውናል።

በቅርቡም በዘመቻው የተገኙ ህገወጥ ተግባራትን ለህብረተሰቡ እንደሚያሳውቁም ሀላፊዋ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡም ህገ ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙት በ8864 የነፃ የስልክ መስመር  እና በአካባቢያቸው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት  እንዳለባቸው በማንሳት

ምግብን ከባዕድ ጋር የመደባለቅ መሰል ህገ ወጥ ተግባራት ተሳታፊ የሚሆኑ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ  እንደሚገባም ሀላፊዋ አሳስበዋል፡፡

ለአለም አሰፋ

ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *