የአብን አባሉ አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከአማራ ክልል የመንግሥት ኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

ላለፈው ሁለት ዓመት ከስምንት ወር ገደማ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን (አባሉ) አቶ ጣሂር ሙሐመድ “በግል ምክንያት” ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ካባለፉት “ሶስት፣ አራት ወራት” ወዲህ አንስቶ ከኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ ላይ ከክልሉ አመራሮች ጋር “በዝርዝር” ንግግር ማድረጋቸውን ያስታወሱት አቶ ጣሂር፤ የክልሉ መንግሥት ጥያቄውን እንደተቀበለው ገልጸዋል።

የቀድሞው የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ፤ “ትንሽ የቤተሰብ ጉዳይ ስለነበረብኝ በቤተሰብ እና በራሴ ጉዳይ ነው የለቀቅሁት” ሲሉ ከኃላፊነት የለቀቁበትን ምክንያት አስረድተዋል።

አቶ ጣሂር፤ “[ከክልሉ አመራሮች ጋር[ በመነጋገር ከፓርቲያችን ሰው ተክተን ነው የወጣሁት” ሲሉም ከኃላፊነት ሲለቅቁ በእሳቸው ቦታ የሚሾም ሌላ የፓርቲው አባል እንዲተካ መደረጉን ገልጸዋል።

በአቶ ጣሂር ቦታ ሌላኛው የአብን አባል አቶ መልካሙ ፀጋዬ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሾማቸውን የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *