ህብረት ባንክ ህብር ማስተር ካርድ የተሰኘ አገልግሎት አስተዋወቀ።

ባንኩ ከማስተር ካርድ ጋር በጋራ በመሆን ነው አገልግሎቱን ያስተዋወቀው።

ባንኩ ኢትዮጵያዊያን በሌሎች የአለም ሀገራት የሚኖራቸውን ግብይት ምቹ በሆነ ሁኔታ እንዲያከናውኑ የሚያስችል አገልግሎት አስተዋውቋል።

አገልግሎቱ የአለም አቀፍ የካርድ አገልግሎት ሲሆን፣ደንበኞች ወደ ውጪ ሀገራት ጉዞ ሲያደርጉ በቀላሉ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት እና በሌሎች ሀገራት በሚኖራቸው ቆይታ ወቅት በማስተር ካርድ አማካኝነት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

ካርዱን ወደ ክፍያ ማሽኖች በማስገባት ወይም በማስጠጋት ብቻ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል እንደሆነ ነው የተገለጸው።

የህብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ከበደ እንደተናገሩት በህብረት ባንክ ውስጥ አጋርነትና ቴክኖሎጂ የእለት ተእለት ተግባራችን ብቻ ሳይሆን የባንኩ የስኬት ጉዞ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የማስተር ካርድ ምስራቅ አፍሪካና የህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ሲኒየር ምክትል ፕሬዝዳንት ሻህርያር አሊ ከህብረት ባንክ ጋር የተደረገው ትብብር በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በመላው አፍሪካ የፋይናንስ አካታችነትና ዲጅታላይዜሽን ዕውን ለማድረግ ያለንን ቁርጠኘነት ማሳያ ነው ብለዋል።

አገልግሎቱ ከክፍያ አማራጭነቱ ባሻገርም ኢትዮጵያዊያን በአለም አቀፍ ገበያ በቀላሉና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መሳተፍ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *