በትግራይ ክልል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች የ17 ወር ውዝፍ ደሞዝ እስካሁን አልተከፈላቸውም ተባለ፡፡

በክልሉ የሚገኙ ሁሉም የጤና ባለሙያዎች የ17 ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው በመቆየቱ ከቤት ኪራይ ጀምሮ በተለያዮ ወጪዎች በእዳ ተይዘው እንደሚገኙ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የፈውስና ተሃድሶ ዋና የስራ ሂደት ተተኪ ዶክተር ስምኦን ገብረጻዲቅ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ባለሙያዎቹ ለመኖር ሲሉ ለሚያስፈልጋቸው ወጪ በብድር ሲጠቀሙ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህም የጤና ባለሙያዎቹ አገልግሎት ለመስጠት ችግር እንደሆነባቸው ጠቅሰዋል፡፡

ሌላው ከጣቢያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የአይደር አጠቃላይ ሪፈራል ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር አብርሃ ገ/እግዚአብሔር እንዳሉት ውዝፍ የ22 ወር የትርፍ ሰአት ክፍያም እስካሁን እንዳልተከፋላቸው አንስተዋል፡፡
ችግሩን የክልሉም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ቢያቁም እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም ብለዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *