ቅርጫ አልተከለከለም!

በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል።

በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገ ጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል።

የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን።

ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *