የጀበና ቡና ሻጯ በትራፊክ አደጋ ህይወቷ አለፈ፡፡

የጀበና ቡና በመሸጥ ህይወቷን ስትመራ የነበረችው ወጣት በደረሰባት የመኪና አደጋ ህይወቷ ማለፉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው እሁድ በፋሲካ እለት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ቡና በመሸጥ ላይ የነበረችው ወጣት ወደ ኋላ እየሄደ በነበረ የኤፌሰር መኪና ተገጭታ ህይወቷ አልፋል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኙኝነት ባለሙያ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በጥንቃቄ ጉለት ወጣቷ ህይወት አልፏል ብለዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ከብቃት ማነስ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በሰው እና በንብረት ላይ የሚያደርሱት አደጋ ቀላል የሚባል አይደልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በትራፊክ አደጋ በርካቶች እንደወጡ ወደ ቤታቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል ያሉት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ እንደ ሃገር ምፍትሔ ሊሰጠው የሚገባ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት በአንድ ሰው ላይ የሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ከጀርባው የበርካቶችን ተስፋ ያጨልማል፣ የሞቀ ቤትን ያቀዘቅዛል እንዲሁም ፈርጀ ብዙ ጉዳትን ያስከትላል ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሚያዝያ 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *