የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለረጅም ዓመታት በግለሰቦች ተይዘው የነበሩ ሼዶች እና በተለምዶ አረከበ ሱቆች የሚባሉትን ተለጣፊ ሱቆች ለ3ተኛ ወገን አሳልፈው የሸጡትን እና ውጤታማ ያለሆኑትን በመንጠቅ ለሌሎች የስራ እድል እየፈጠረበት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ ማስፋፍያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰብሃዲን ሱልጣን ለጣብያችን እንደገለፁት ከ2ሺህ በላይ ሼደች መንጠቁን ገልፀው በፍርድ ቤት ያሉ ኬዞችንም በመርታት የማጥራት ስራ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
አዲስ መመሪያ ወርዶ ወደ ስራ መገባቱን የገለፁት ዳይሬክተሩ የመንጠቅና ወደ መንግስት የማስገባት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ለ3ተኛ ወገን የሸጠውን አካል በመንጠቅ ለሚመለከተው አካል የማስተላለፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመዲናዋ አዲስ አበባ ለስራ አጥ ወጣቶች ተላልፈው ረጅም ግዜ በስራ ላይ ከሚገኙት የመስሪያ ቦታዎች በተለምዶ የአርከበ ሱቆች የሚባሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ተለጣፊ ሱቁ ወይም በተለምዶ አርከበ ሱቅ የሚባለው በ1997 እንዲሁም ከዛ በፊት በሊዝ ለወጣቶች ተላልፎ የተሰጠ ቢሆንም አሁንም ድረስ ሳይሸጋገሩ መቆየታቸው ተነግሯል፡፡
በአቤል ደጀኔ
ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም
