17 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ የፀጥታ ችግር ተከስቶ እንደነበር የክልሉ ፕሬዜዳንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰጡት መግለጫ፤ ” በክልሉ በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉን የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌዴራል የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ ስራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል ” ብለዋል።
በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌዎች በሚኖሩ ግለሰቦች መካከል የተነሳዉ አለመግባባበት ወደ ግጭት ማምራቱን የገለፁት የክልሉ ፕሬዜዳንት በዚህም በወረዳውና በጋምቤላ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።
በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የዘጠኝ (9) ሰው ህይወት ሲያልፍ 17 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ መከናወኑን አመልክተዋል።
