የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ መስቀል መስቀል በትዊተር ገጻቸው ላይ “ኤርትራ በኢጋድ ውስጥ የጀመረችውን እንቅስቃሴ ቀጥላለች እና መቀመጫዋንም ይዛለች ”ብላዋል፡፡
ሚኒስትሩ ሀገራቸው “ሰላም፣ መረጋጋትና ቀጠናዊ ውህደት” ላይ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።
ኢጋድ በ2007፣ ኬንያ የኢትዮ- ኤርትራን የድንበር ውዝግብ እንድትመለከት ውሳኔ ሲያሳልፍ ኤርትራ ከድርጅቱ አባልነት መውጣቷ ይታወሳል፡፡
የኢጋድ ዋና ጸሓፊ ወርቅነህ ገበየሁ ኤርትራ ወደ ህብረቱ መመለሷን አወድሰውታል ሲል የአሜሪካ ኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ሰኔ 06 ቀን 2015 ዓ.ም
