የጸደይ ባንክ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መኮንን የለዉምወሰን የተደረገዉ ስምምነት ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ የሚያስችል እንደኾነ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንተርፕራይዞች በሀገር እድገት እና ልማት ላይ ያላቸዉ ድርሻ ከፍተኛ በመኾኑ በፋይናንስ ሊደገፉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተለይም ወጣቶች በሥራ ፈጠራ ስኬታማ እንዲኾኑ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚዉ፣ ባንኩ ወደ ባንክነት ከማደጉ በፊትም ሥራ ፈጣሪዎችን ሲደግፍ ቆይቷል ብለዋል፡፡ ይህንንም ለማስቀጠል እንሰራለን ማለታቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል፡፡
የአሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ቴክኖሎጂ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማዉ አጥናፉ “አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማፍራት በሚደረገዉ ጥረት በጋራ እንሠራለን” ብለዋል።
በሃገራችን የባንኮች የፋይናንስ ተደራሽነትን በተመለከተ ብዙሃኑን ገና ተጠቃሚ ማድረግ አልቻሉም የሚል ትችት ይቀርብባቸዋል፡፡
በተለይም ወጣቶችና የገጠሩ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽነት ላይ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የዘርፉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም
