ወደ ጎረቤት ሀገር ሊሻገር የነበር አደንዛዥ እፅ፣የዝሆን ጥርስ፣ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሊሻገር የነበረ አደንዛዥ ዕፅ ፣የዝሆን ጥርስ ፣ደረቅ ጫት እና ነዳጅ በሁመራ ከተማ ፣ዲማ ፣ ባዕከር እና ራዊያን ኬላ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል፡፡

የሃገር መከላከያ ሰራዊት በኬላዎችም ይሁን በሌላ መንገድ የሚዘዋወሩ ህገ-ወጥ ዝውውሮችን በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ሀገራዊ ግዴታችንን እየተወጣን እንገኛለን ብሏል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ መነሻውን ከሻሸመኔ ያደረገ እና ወደ ሱዳን ሊሻገር የነበረ 22 ማዳበሪያ አሽሽ ፣ መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገ በቁጥር 25 ፍሬ ኮኬን አደንዛዥ ዕፅ ፣ ባለ 25 እና 20 ሊትር 42 ጀሪካን ነዳጅ ፣ 19 ካርቶን ደረቅ ጫት እንዲሁም አራት የዝሆን ጥርስ መያዙን ገልጻል፡፡

ህገ ወጦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት ሲሆን ጥብቅ ክትትል ሲደረግባቸው የቆየ መሆኑንም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *