ሚንስትር ዴኤታው የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል በሀገር ደረጃ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመቅረፅ ለአራት ዓመታት ተግባራዊ እያደረገ እንደሆነም ተናግረዋል።
ስትራቴጂክ ዕቅዱ መተግበር በጀመረ በተከታታይ ሁለት ዓመታት በየዓመቱ ለ3ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ፣ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሀገሪቱ ባጋጠሙ ልዩ ልዩ ችግሮች ምክንያት ስትራተጂክ ዕቅዱን መተግበር አለመቻላቸውን ሚኒስቴር ድኤታዉ አስታዉቀዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በስራ ዕድል ላይ አስራ አንድ ዘርፎችን ለይቶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ ዋነኛዉ የስራ ፈጠራ መሆኑን ገልፀዋል።
ተቋሙ ዕቅዱን ማሳካት የሚያስችለዉ የስራ ፈጠራ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑ የገለፁት አቶ ንጉሱ ሁሉም በጋራ የስራ ፈጠራ ላይ ተባብሮ ከስራ በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሰላም ኢትዮጵያ ግብረሰናይ ድርጅት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን ባስጠናዉ ጥናት የፈጠራ ዘርፉ ያሉበትን ክፍተቶች መለየት እንዳስቻላቸዉ ተናግረዋል።
በዚህም ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በተለይም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን የፈጠራ ዘርፉን ለስራ ዕድል ፈጠራ አጋዥ በሚሆንበት መንገድ ላይ ስራዎች እየተሰሩ ናቸዉ ብለዋል።
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እ.ኤ.አ በ2030 ለ20ሚሊዮን ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍር እየሰራ መሆኑንም ሚኒስቴር ዲኤታዉ አስታዉቀዋል።
በአቤል ደጀኔ
ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም
