የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የሳዑዲ ዓረቢያ የድንበር ጠባቂዎች ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን በየመንና ሳዑዲ ዓረቢያ ድንበር ላይ በጅምላ ገድለዋል በማለት ሂውማን ራይትስ ዎች ያቀረበውን ክስ፣ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር “በአስቸኳይ” እንደሚያጣራ አስታውቋል።
ሚንስቴሩ፣ መንግሥት ጉዳዩን “እየተከታተለው” እንደኾነና የምርመራውን ውጤትም እንደሚያሳውቅ የገለጸ ሲኾን፣ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ከ”አላስፈላጊ ግምቶች” መቆጠብ እንደሚገባ አሳስቧል።
ስማቸው ያልተጠቀሰ የሳዑዲ ባለሥልጣናት ውንጀላውን “መሠረተ ቢስ” እና “በታማኝ ምንጮች ላይ ያልተመሠረተ’ በማለት እንዳጣጣሉት Afp ዘግቧል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሃሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም
