ጀንቦሮ ሪል ስቴት በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላ ሁለተኛውን የሪልስቴት ኘሮጀክት ነው ያስመረቀው።
በዛሬው ዕለት የተመረቀው ሁለተኛው ኘሮጀክት 72 መኖሪያዎችን የሚይዝ በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው ተብሏል።
ለባለቤቶቹ የተላለፉት እነዚህ ቤቶች 6 መቶ70 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል ነው የተባለው።
ለህንፃው አገልግሎት የሚሰጡ የከርሰ ምድር ውሃ፣ሊፍት፣የደህንነት ካሜራዎችና ጀነሬተር እንደተገጠመለትም ሰምተናል ።
“በጊዜ ግቡ” በሚል መሪ ቃሉ የሚታወቀው ጀንቦሮ ሪል ስቴት በ2012 ዓ.ም የተመሠረተ ነው።
በቀጣይ በሳርቤት ሳይት 5ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍ የመኖሪያ መንደር እንደሚገነባም ገልጿል ።
በመጪው አምስት አመታት ውስጥ 5000 አፖርትመንቶችን ፣ ቪላዎችን እና የንግድ ስቆችን ለቤት ገዥዎች በጥራት ሰርቶ ለማጠናቀቅ ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል።
በአባቱ መረቀ
ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም
