የገንዘብ ሚኒስቴርና የዓለም ባንክ ለአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ኮሪደር ፕሮጀክት (በኢትዮ-ጅቡቲ ኮሪደር ፕሮጀክት) የ730 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን 90 በመቶ የባህር ንግድን የሚይዘው ስትራቴጂካዊው ከአዲስ አበባ-ጅቡቲ ኮሪደር ጋር በተሳሰረ መልኩ የኢትዮጵያን የሎጅስቲክስና የትስስር አቅም እንደሚያጎለብት ተገልጿል።

በስምምነቱ መሰረት ለሜኦሶ-ድሬዳዋ መንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን ግንባታው የትራንስፖርት አቅምና ብቃት የሚጨምር መሆኑንም የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።

መንገዱ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎች የጤና፣ ውሃና ትምህርት አገልግሎት ተደራሽነት ጨምሮ ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክቷል።

ፕሮጀክቱ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሺዬቲቭ አካልና የቀጣናዊ ትብብር ማዕቀፍ እንደሆነ ያመለከተው ሚኒስቴሩ ማዕቀፉ አካባቢውን በመሰረተ ልማት የማስተሳሰር ፋይዳም እንዳለው ተጠቅሷል።

ስምምነቱን የተፈራረሙትም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ የቀጣናዊ ትስስስር ዳይሬክተር ቡቴይና ጉርማዚ ናቸው።

የገንዘብ ሚኒስትርና የወቅቱ የሆርን ኦፍ አፍሪካ ኢኒሺዬቲቭ ሊቀ-መንበር አቶ አህመድ ሺዴ ለዓለም ባንክ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ ትስስር መጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል።

የመሰረተ ልማት እድገት ለቀጣናው የረጅም ጊዜ ልማትና መረጋጋት ወሳኝ አስተዋጽኦ እንዳለውም መገለጹን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *